2009-08-12 13:34:26

የሚከሰት ቀውስ ለተስተዋለ መፍትሔ እና ለአዲስ እቅድ አጋጣሚ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር በደረስዋት ዓዋዲት መልእክት “ባለማችን ተከስቶ ያለው ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ለተስተዋለ እና ለአንድ አዲስ እቅድ አጋጣሚ መሆን አለበት” RealAudioMP3 በማለት ያሰፈሩት ሃሳብ የዓለም የሥነ ምግባር ባንክ ቤት ሊቀ መንበር ፋቢዮ ሳልቪያቶ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅሰው፣ የዓለም አቀፍ የኤኮኖሚው ስልት ዳግም ተከልሶ ለአዲስ የኤኮኖሚ ሂደት እና ስልት ፈር መሆን አለበት ብለዋል።

የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ፣ መንግሥት ማኅበረሰብ እና ገበያ በተሰኙት ሦስት ምሰሶዎች ላይ የጸና መሆን እንዳለበት የር.ሊ.ጳ. ዓዋዲት መልእክት እንደምታመለከትም አውስተው፣ ስለዚህ በነዚህ ሦስት ምሰሶዎች መካከል ግኑኝነት መኖር አለበት፣ አንዱ ለብቻው ተነጥሎ መራመድ የለበት፣ እንዲህ ካልሆነ ግን ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመላቀቅ ፈጽሞ አዳጋች ይሆናል። ስለዚህ ሰውን ማእከል ያደረገ ሥነ ምግባር የሚከተል የኤኮኖሚ ሥልት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው ያሰፈሩት ሓሳብ የዓለማችን ባህል መታደስ እንዳለበት የሚያስገነዝብ ጥሪ መሆኑ አብራርተዋል። ለሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች አጥጋቢ እና ተጨባጭ ምላሽ መስጠት ማለት ድኽንነ መዋጋት፣ ተፈጥሮን ማክበር ማለት መሆኑ አስገንዝበዋል። በመጨረሻ እኚህ የዓለም አቀፍ የሥነ ምግባር ባንክ ቤት ሊቀ መንበር ይላሉ “ቅዱስ አባታችን ፍቅር በሐቅ በተሰየመቸው አዋዲት መልእክታቸው አማካኝነት ለዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ባለ ሙያዎች ለመንግሥታት እና ለኅብረተሰብ አቢይ መመሪያ ነው የሰጡት። ቅዱስነታቸው ለሚያምንም ለማያምንም መከተል የሚገባውን መንገድ አመልክተዋል፣ ትርፍ ብቻ ሳይሆን ሥነ ምግባርን የሚያከብር ወይንም የሚከተል ዓይነት ትርፍ የማግኘት ሥርዓት መኖር እንዳለበት ር.ሊ.ጳ. በጻፉዋት ዓዋዲት መልእክት ያሰመሩበትን ሐሳብ ለጠቅላላው የኤኮኖሚ ሂደት ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የፍትሕና ትብብር ድርገት በኤኳዶ ርእሰ ከተማ ኪቶ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 3 ቀን እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር የተደረሰቸው የር.ሊ.ጳ. አዋዲት መልእክት መሠረት አካባቢ እና በጠቅላላ ተፈጥሮን የማክበር ኃላፊነት እና ግዴታ በተመለከተ የሠፈረው ሰፊ እና ጥልቅ ሐሳብ በማስደገፍ ውይይት ማካሄዱ ተገለጠ።

የሰው ልጅ ለማምረት ወይንም ለፍጆት የተፈጠረ ኤኮኖሚያዊ መሆን እንደሆነ ብቻ አድርጎ የሚመለከተው የኤኮኖሚ ሂደት በሰውን ልጅ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮም ላይ ያስከተለው እና እያስክተለው ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር፣ ድኽነትን ያካባቢ ተፈጥሮ ብከላ ብሎም ለተለያየ ግጭት የሰብአዊ መብት ረገጣ ወዘተረፈ ለመሳሰሉት አቢይ ባህላዊ ቀውስ ምክንያት መሆኑ የላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያ ብጹዓን ጳጳስት የፍትሕ እና የትብብር ድርገት ባካሄደው ስብሰባ ባጸደቀው የማጠቃለያ ሰነድ በማመልከት፣ “ዓለማችን የሚከተለው የኤኮኖሚ ስልት የሰው ልጅ እንደ ማእከል እና ግብ ወይንም ፍጻሜ ሳይሆን እንደ ማንኛውም የተፈጥሮ ጸጋ ለምርት የሚያገለግል እና ሃብት የማካበቻ መሣሪያ አድርጎ መጠቀም የሚያመመለክት በመሆኑ በድኾች አገሮች ይቅርና በበለጸጉት አገሮች ጭምር በማእከላዊ ደረጃ የሚተዳደረው ህዝብ ወደ ድኽነት እንዲያሽቆለቁል እያደረገው ነው። ስለዚህ የዓለማችን የኤኮኖሚ ሂደት የተፈጥሮ ሃብት የሁሉም ለሁሉም መሆኑ የተገነዘበ የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት ለማርካት ያነጣጠረ ለመተባበር ለመቀራረብ እና ለመከባበር የሚያነቃቃ መሆን እንደሚገባው ሰነዱ በማመልከት፣ ከዚህ ውጭ የሆነ የኤኮኖሚ ስልት ለጥፋት ብቻ መሆኑ በሰነዱ ተብራርቶ፣ በመጨረሻም የተሟላ የሰው ልጅ እድገት የሚያስገኝ በእግዚአብሔር የተፈጠረውን ሕይወት እና የተፈጥሮ ሃብት ማክበር መሆኑ ሰነዱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.