2009-08-12 13:38:22

አልፋታህ


አል ፋታህ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የፍልስጥኤም ታሪካዊው የፖለቲካ ሰልፍ በቤተልሔም ከተማ ጉባኤው እያካሄደ መሆኑ ተገለጠ። በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ያመራር አባላቱን ለመምርጥ ድምጽ መሰጠቱ ለማወቅ ሲቻል፣ RealAudioMP3 እንደሚባለውም ሰፊ ድምጽ ያገኙት በእስራኤል ወህኒ ቤት የሚገኙት 50 ዓመት እድሜ ያላቸው ዓለም በቃኝ ፍርድ የተበየነባቸው ማርዋን ባርጉቲ መሆናቸውም ሲገለጥ። ባርጉቲ በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ያላቸው ተወዳጅነት እና ተቀባይነትም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩት ያልፋትህ ታሪካዊው መሪ እና የፍልስጥኤም ራስ ገዝ ብሔራዊ መንግሥት ርእሰ ብሔር ከነበሩት ከያስሪ አራፋት ያላነሰ መሆኑ ሲነገር፣ ያስሪ እራፋትን ይተካሉ ተብሎም ይነገርላቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.