2009-08-12 13:35:49

ስደት እና ስደተኛ


ከተለያዩ አገሮች በተለያዩ ማህበራዊ ኤክኖሚያዊ ሰብአዊ እና ፖሊቲካው ብሎም ሃይማኖታዊ መሠረት ባላቸው ችግሮች ተገፋፍቶ ወደ ኤውሮጳ የሚጎርፈው የሕገ ወጥ ስደተኛ የሚያጋጥመው የሞት አደጋ አሳሳቢ መሆኑ እና RealAudioMP3 በሁሉም ዘንድ ችላ መባል የሌለበት አሳዛኝ አጋጣሚ መሠረት በማድረግ ስለ እነዚህ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ የሚከራከር ፍሮትረስ ኤውሮጳ የተሰኘው ማህበር፣ ባንዲት አነስተኛ ጀልባ ተሳፍረው ወደ ኢጣሊያ ለመግባት ሲሞክሩ በደረሰባቸው አደጋ ሳቢያ የሰጠሙት እና ገና አስከሬናቸው በመፈለግ ላይ ያሉትን የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ በማስመልከት ኤውሮጳ ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ ችላ ማለት አይገባትም ብለዋል።

የዚህ ፎርትረስ ኤውሮጳ ማኅበር መሥራች ጋብሪኤለ ደ ግራንደ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ወደ ኢጣሊያ የሚጎርፈው የሕገ ወጥ ስደተኛው ብዛት ዝቅ እያለ ነው ማለት፣ ወደ ሌሎች የኤውሮጳ አገሮች የሚጎርፈው የስደተኛ ብዛት ቀንሰዋል ማለት አይደለም” ብለዋል።

“አለ ምንም ችግር ቤቱን እና ንብረቱ ቤተሰቡን እና አገሩን ጥሎ የሚሰደድ ሰው የለም፣ ስለዚህ እርዳኝ ብሎ ድንበርህን አቋርጦ ለመጣብህ ወደ መጣበት መሸኘት ለሚደርስበት አደጋ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠያቂ ያደርግሀል፣ የፖለቲካ የኤኮኖሚ ችግር ገፋፍቶት በሰብኣዊ መብትና ፈቃድ ረገጣ ችግር ጥገኝነት የሚጠይቅ ብዙ አለ፣ ስለዚህ የያንዳንዱ ስደተኛ ጉዳይ አንድ በአንድ አዳምጦ እና አጢኖ በሁለትዮሽ መንግሥታት ውል ተደግፎ ሳይሆን፣ በአለም አቀፍ ውል መሠረት ምላሽ መስጠት ሰብአዊ እና ፖለቲካዊ ኃላፊነት መሆኑ ታምነው ሁሉም መንግሥታት በማክበር ተገቢ ምላሽ መስጠት ግዴታ አለባቸው። ለኤውሮጳ ኤኮኖሚ የውጭ ሰው ጉልበት እጅግ ያስፈልገዋል፣ እውነትም ነው፣ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ስደተኛውን ለመቀበል ብቸኛ መሠረታዊ ምክንያት አድርጎ መመልከቱ ትልቅ ስህተት እና ስግብግበነት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.