2009-08-12 13:37:13

ምሥራቅ እስያ


ማራኮት የሚል መጠሪያ ተሰጥቶት ባለው ኃይለኛው ዓውሎ ነፋስ የተቀላቀለበት ዝናብ የእስያ ምሥራቃዊ ክልል አገሮች እጅግ መጠቃቱ ሲገለጥ፣ በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ በብዛት የታይዋን እና የፊሊፒንስ ዜጎች የሚገኙባቸው በጠቅላላ RealAudioMP3 80 ሰዎችን ሕይወታቸውን እንዳጡ ለማወቅ ተችለዋል። 6.4 ሪኽተር በተለካው ርእደ መሬት በተጠቃቸው እና 13 ሰዎች ለሞት አደጋ የተጋለጡባት ጃፓንም ሳትቀር በዚህ ዓውሎ ነፈሳ መጠቃቷ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

ዝናብ አዘል ኃይለኛው አውሎ ነፋስ አሁንም በቻይ በፊሊፒንስ እና በታይዋን የባህር ዳርጃ ክልሎች ለጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እያጋለጠ መሆኑ ተገልጠዋል። በቻይና ከፍተኛ የውኃ መጥለቅለቅ አደጋ ከመከሰቱም ባሻገር፣ በአገሪቱ ደቡባዊው ምሥራቅ ክልል የሚኖረው ህዝብ ለከባድ አደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ እና አንድ ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ቤቱን እና ንብረቱን ጥሎ ለመፈናቀል አደጋ መዳረጉ የሚዘከርም ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.