2009-08-10 14:07:58

ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ባለፉት ቀናት በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ በዚህች አገር ርእሰ ብሔር ካቢላ እና በሩዋንዳ ርእሰ ብሔር ጋማሜ መካከል በአገሮቻቸው ሰላም ለማስፈን RealAudioMP3 አቅደው ያካሄዱት የጋራው ውይይት አድንቀዋል።

በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክልል የሚታየው ግጭት እና አመጽ በብዙ ሺሕ የሚገመተው ያገሪቱ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ተመሳሳዩ ችግር በሰሜናዊው የኩቩ ክልል ጭምር እየታየም ሲሆን፣ ይህ ክልል ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች አጋልጦ ያለው በኮንጎን መደበኛ ሰራዊት እና የሩዋንዳ ዴሞክራሲያዊ ግንባር መካከል ተከስቶ ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉት ግኑኝነቶች ማበረታታት እጅግ እንደሚያስፈልግ ባን ኪ ሙን አስታውቀዋል።

በኮንጎ ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፍናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት ተጠሪ ፍራንቸስካ ፎንታኒኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ ክልል ግጭት በነዚህ ባለፉት ስምንት ወራቶች ውስጥ ብቻ 400 ሺሕ የክልሉ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ አውስተው፣ ለመፈናቀል አደጋ ለተጋለጠው ሕዝብ ድጋፍ ለማቅረብ በክልሉ ያለው ውጥረት አቢይ እንቅፋት መሆኑ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.