2009-08-10 14:10:15

የቨነዝዋላ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መገልጫ


የቨነዝዋላ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአገራቸው ስለሚታየው አንዳንድ የፖለቲካው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ አስታውቀዋል። የዚህ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የማራካይቦ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኡባልዶ ሳንታና ሰከላ ፊርማ የሰፈረበት መልእክት እንደሚያመለክተው፣ “የበጋው ዕረፍት እራስህን ለማደስ የሚያገለግል ወቅት መሆኑ ሲታወቅ፣ የዕረፍቱ ወቅት በሚገባ ተጠቅሞ ህዝ RealAudioMP3 ብንና አገርን በሚገባ ለማገልገል፣ ሁሉም በተሰማራበት ሞያ ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም ለመጠመድ የሚያግዘው መልካም ግፊት የሚያረጋገጥበት፣ ለመልካም ዓላማ ቁርጥ ፈቃድ ለማድረግ የሚያግዝ ሲሆን፣ የፖልቲካው ዓለም ዜጎች በእረፍት ላይ መሆናቸው በመገንዘብ አጋጣሚውን ተገን በማድረግ ችኩል ውሳኔ ለማስተላለፍ ሲራወጡ መታየቱ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ በመግለጥ፣ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ነው” ብለዋል።

በቅርቡ የአገሪቱ መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ላይ የወሰደው ውሳኔ፣ የኅብረ መገናኛ ብዙኃን ገጽታ የሚቀናቀን የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት የሚሰርዝ መሆኑ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም ያላቀና ውሳኔ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ጭምር በማብራራት፣ ስለዚህ የፖለቲካው ዓለም የሚያስተላልፈው ውሳኔ ዓላማው የዜጎች እና የአገር ጥቅም ያነጣጠረ መሆን እንደሚገባው ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልክት አበክረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.