2009-08-10 14:11:40

ብሔራዊ የቤተሰብ ሳምንት


በብራዚል በጠቅላላ ቁምስናዎች ብሔራዊ የቤተሰብ ሳምንት “ቤተሰብ፣ ቤተክርስትያን፣ የሓዋርያነት ፈር” በሚል ርዕስ ሥር እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ የብራዚል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እያከበረቸው ባለው የትምህርተ ክርስቶስ ዓመት RealAudioMP3 መሠረት እየተመራ ያለው ብሔራዊው የቤተሰብ ሳምንት በማስደገፍ የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥር የሚመራው የሕይወት እና የቤተሰብ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ኣቡነ ኦርላንዶ ብራንደስ ይላሉ፣ “እያንዳንዱ ቤተሰብ ሓዋርያዊ ልኡክ መሆኑ ነው፣ ወላጆች ለልጆቻቸው በቃልና በሕይወት የወንጌል ምስክሮች መሆን እንዳለባቸው አደራ” በማለት፣ “እያንዳዱ ቤተሰብ ቤታዊ ቁምስና ነው” ብለዋል።

የዚህ የብራዚል ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሕይወት እና የቤተሰብ ጉዳይ የሚንከባከበው ድርገት ዋና ጸሓፊ አባ ሉዊስ አንቶኒዮ በንቶ፣ “ይህ ብሔራዊው የቤተሰብ ሳምንት የቤተሰብ መሠረት የሆነው ሚሥጢረ ተክሊል የሚጎላበት እና በዚሁ ቅዱስ ሚሥጥር ዙርያ ሰፊ አስተንትኖ የሚደረግበት መሆኑ” አውስተው፣ “እያንዳንዱ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ቃል በመደጋገፍ ወዳጅነት እና መቀራረብ የሚመሰክርበት ቀዱስ ሳምንት ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.