2009-08-10 14:06:48

በምሥጢረ ተክሊልና በምሥጢረ ተክሊል አልባነት አብሮ መኖር


ቤተሰብ ሁለት ሰዎች በመስማማት በሚኖሩት የአብሮ መኖር ምርጫ የሚቋቋም ማለት እንዳልሆነ በኢጣሊያ ሮማ ከተማ የሚገኘው የሉምሳ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የስነ ሕግ ሊቅ ፕሮፈሶር ጁዘፐ ዳላ ቶረ ስለ ትዳር እና ሚሥጢረ ተክሊል RealAudioMP3 በሚል ርእስ ሥር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ ሁለት ሰዎች፣ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በመስማማት አብረው በመኖር የሚመሠረቱት ቤተሰብ እና በሚሥጢረ ተክሊል የሚቋቋመው ቤተሰብ መካከል ዓቢይ ልዩነት እንዳለ ሲገልጡ፣ “ይህ ልዩነት በሥነ ሕግ አንጻር ብቻ ሳይሆን በተጨባጩ ያኗኗር ስልት አንጻርም ሲታይ ልክ በሚሥጢረ ተክሊል አማካኝነት እንደሚመሠረተው ቤተሰብ በግልና በማህበራዊ ደረጃ የሚኖር ኃላፊነት የለውም፣ በሚሥጢረ ተክሊል የሚጸናው ውህደት እስከ ፍጻሜ ሲሆን፣ በመተማመንና በመከባበርን የተሸኘም ነው፣ በመስማማት አብሮ አለ ሚስጢረ ተክሊል መኖር ዘለቄታ ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፣ ሆኖም ግን ኃላፊነት የተላበሰ የሕይወት ምርጫ አይደለም፣ ያለው ኃላፊነትም እጅግ ኮሳሳ ነው” ብለዋል።

ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤኒዮ አንቶኔሊ “ቤተሰብ ማኅበራዊ ኃላፊነት ያለው የሕይወት ምርጫ ሆኖ፣ በእግዚአብሔር እና በማኅበረሰብ ፊት የሚወሰድ የውህደት ኃላፊነት ነው። ይህ ውህደት እንዳሻህ የሚመሠረት ወይንም የሚፈርስ ጉዳይ አይደለም፣ ሚሥጢረ ተክሊል የአንድ ቤተሰብ ግላዊ እና ማኅበራዊ ኃላፊነትን ያጎላል፣ ተዋደናል ስለዚህ አብረን እንኑር ከሚለው አመለካከት የሚመሠረተው ያብሮ የመኖር ምርጫ አብረው በሚኖሩት መካከል ውህደት ሊኖር አይችል፣ ስለዚህ ውህደቱ ከሌለ ደግሞ የጋራ ኃላፊነት የማይጎላበት የሕይወት ምርጫ ይሆናል። ማኅበራዊም ሆነ ግላዊ ኃላፊነት የሌለው በመሆኑም ከዚህ ዓይነት ምርጫ ከሚመሠረተው ቤተሰብ የሚወለዱት ሕጻናት ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ችግሮች የተጋለጡ ይሆናሉ” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.