2009-08-10 14:09:12

ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ


ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ሁለት የጃፓን ከተሞች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ሰለባ የሆኑበት 64ኛው ዓመት በመዘከር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ በኢጣሊያ የሳይንስ ሊቅ ፕሮፈሰሮ አንቶኒዮ ዚኪኪ፣ RealAudioMP3 በአሁኑ ወቅት ዓለማችን ለዚህ አደገኛው ቦምብ ምን ያክል መጋለጧ እና ያለውም ስጋት ምን ያክል እንደሆነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ “የአቶሚክ ቦምብ መርኃ ግብር ኃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች እጅ እስካለ ድረስ ሥጋቱ የማይቀር ነው፣ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ አገሮች በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ ከተጣለው አቶሚክ ቦምብ እጅግ አደገኛ የሆነ ቦምብ ባለ ቤት መሆናቸውም ዘክረው፣ አንዳንድ አገሮች ያላቸው የቴክኖሎጂ ዕድገት ደረጃ በተመለከተ የሚታወቅ ነገር የለም፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ያለው ሥጋት ለመገመቱ አያዳግትም፣ የኑክሊየር የጦር መሣሪያ የዕልቂት እና የጦርነት ኃይል ሲሆን፣ የኑክሊያር ሃይል ምንጭ ግን የሰላም መሣሪያ ነው፣ ስለዚህ የኑክሊየር ኃይል ለክፋት ለጥፋት ወይንም ለመልካም ዓላማ ማስፈጸሚያ ሊውል ይችላል፣ ይህ ጉዳይ የባህል እና የሳይንስ ዘርፍ የሚመለከት ነው” ምክንያቱም ይላሉ “የፍቅር የወንድማማችነት የሕይወት ባህል ከተስፋፋ፣ የኑክሊየር ኃይል ለመልካም ዓላማ ሊውል ይችላል፣ የጥላቻ እና የሞት ባህል ከተስፋፋ ደግሞ የኑክሊየር ኃይል ለአደገኛ ዓላማ ማስፍፈጸሚያ እንደሚውል አያጠራጥርም” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.