2009-08-10 15:58:48

በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ በአመሪካ.


በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳዮች ምክትል ሐላፊ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ ለጉብኝት በዩናይትድ ስቴትስ እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን በኢንድያና ክፍለ ሀገር በሚገኘው ኖትረ ዳም ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ በዚሁ የአመሪካ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ለተማሪዎች እና ለዩኒቨርሲቲው ፕሮፈሰሮች እንደገለጡት ፡ ኤውሮጳ ራስዋ እና ማንነትዋ ለማግኘት ከፈለገች ክርስትያን መሆንዋ አምና መቀበል እና ገቢራዊ ማድረግ አለባት ።

የኤውሮጳ ከክርስትና መገለል እና የእግዚአብሔር ሕግ አለታዘዝም ማለት ለኤውሮጳ አሉታዊ መሆኑ ያመለከቱት ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ ፡ ከሞራል ተገንጥሎ የሚካሄደው ድርጊት ለኤኮኖሚ ለፖሊቲካ ይሁን ለተክኖሎጂ እድገት ሊያመጣ እንደማይችል ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ማመልከታቸው ተገልጠዋል።

የሰው ማንነት ማታቀብ ሲገባው ከእግዚአብሔር ለመራቅ የሚደረድገው መፍጨርጨር ጐጂ እንጂ ጠቃሚ ሊሆን እንደማይችል ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ በኢንድያና ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው መግለጣቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

ሥነ ምግባር ያለው ተፈጥሮአዊ ቤተሰብ ማኅበረሰብ እና ኅብረተሰብ ቀጥ አድርጎ መያዝ ሲገባ በተለያዩ ሽፋኖች እነሱን እንዲበተኑ የሚደረገው አሉታዊ ተግባር መገታት እንደሚያሻም ብፅዕነታቸው ማሳሰባቸው ተመልክተዋል።

በአሁኑግዜ የክርስትና እሴቶች ባለቤት በሆነችው ኤውሮጳ እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ የመኖር ዘይቤ አሳሳቢ እተሆነ መምጣቱ በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ሊቀጳጳሳ ብፁዕ አቡነ አማቶ በኖትረዳም ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ከደረጉት ንግግር ለማወቅ ተችለዋል።

ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ አነጀሎ አማቶ ንግግራቸው በማያያዝ ፡የእግዚአብሔር ልዓላውነት መጣቀሻ ያላደረገ ዓለማውነት ሰብአዊ ክብር ነጻነት ፍትሕ እና ትብብር ማእከል ያደረገ ሊሆን እንደማይችል ማስገንዘባቸው ከዩኒቨርሲቲው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ብፁዕ አቡነ አማቶ ፡ የኤውሮጳ ሕብረት ሕገ መንግሥታት አስታውሰው ፡ እግዝአብሔርን መጣቀሻ የማያደርግ ሕገ መንግሥት የኤውሮጳ መንነት የሚያደበዝዝ ሳይሆን ጭራሽ የሚደምስስ እንደሆነ መግለጣቸውም ተያይዞ ተመልክተዋል።

ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በየዓለማውነት የፖሊቲካ ርእዮተ ዓለም ጣልቃ ለመግባት ባትሻም ዘወትር ዓለማውያን መንግስታት ከእግዚአብሔር እንዳይገለሉ ማሳሰብዋ እንዳልቀረ ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

በመጨረሻም ኤውሮጳ የሰው ዘር መሠረታዊ መብቶች ለመጠበቅ የምትሻ ከሆነ መንነትዋ ከክርስቶስ ስቅለት እና ከሕገ ሙሴ ጋር የተሳሰረ መሆኑ መዘንጋት የለባትም ማለታቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.