2009-08-07 20:11:40

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ዕረፍት 31ኛው መታሰቢያ ዓመት ተከበረ


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ እአአ ከ31 ዓመታት በፊት ነሐሴ 6 1978 ዓ.ም. ምሽት ደብረታቦር በዓል ቀን በካስተልጋንደልፎ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወቅት መኖሪያ ሐዋርያዊ አደራሽ ውስጥ ማረፋቸው በታሪክ ማኅደራቸው ተመዝግቦአል። ይህንን ዕረፍታቸውን ለማስታወስ የቫቲካን ህየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ ትናንት ከቀትር በኋላ 5 ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማቅረባቸው ተመልክቶአል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ለፍጻሜ በማብቃታቸው ቤተ ክርስትያንን ደግሞ ለረጅም ዓመታት በጥበብና በአርቆ አሳቢነት በመምራታቸው ይዘከራሉ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ለሓቅና ለእውነት ፍቅር አንዳንዴ በሰዎች ዘንድ የተጠሉ ውሳኔዎች በማድረጋቸውም ይታወሳሉ። RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.