2009-08-05 17:11:59

ቅዱስ አባታችን ለስደተኞችና ለተፈናቀሉ ጸሎት እንዲደረግ ተማጥነዋል


የርሊጳ የነሐሴ ወር የጸሎት ሐሳብ በስደተኞችና በተለያየ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉት ያተኮረ ነው። ቅዱስነታቸው በጸሎቱ ማቅረቢያ ምእመናን ሁሉ: “እግዚአብሔር የዓለም ሕዝብ ሁሉ ኅሊና በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰደተኞችና ተፈናቃዮች ችግር  በመረዳት ለዚሁ አሰቃቂ ችግር  መፍትሔ የሚሆን ሁነኛ እርምጃ እንዲያደርጉ ይረዳቸው ዘንድ” እንዲልምኑ ተማጥነዋል።
ይህን በተመለከተ በኢየሱሳውያን የሚተዳደር እስታሊ የስደተኞች ማእከል ፕረሲደንት ኣባ ጆቫኒ ላማና ለቫቲካን ረድዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “ቅዱሱ ኣባታችን ለ42 ሚልዮን የሚያህሉ የዓለም ስደተኞች እንድንጸልይ ጥሪ በማቅረብ ሲደግፉን ደስ ይለናል። ይህ ጥሪ የዓለማችን ቸግሮችን ለመለወጥ ኃላፊነትና ሥልጣን የያዙትን ሰዎች ኅሊና መቀስቀስ አለበት። እነኚህ ችግሮች የሚያሳስቡን እንደ አማኞች መጠን ቢሆንም ቅሉ፣ የሰው ልጅ መብት ሲረግጥ ዝም ብሎ መመልከትም በኃላፊነት የሚያስጠይቅ ነው። የጣልያን መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የሚያደርገውን የተመለከትን እንደሆነ፣ የጀነቭ አገር አቀፍ የስደተኞች ስምምነት ፈራሚ ብትሆንም ቅሉ ስደተኞች ሃገሪቱ ከመግባታቸው በፊት ስለምትገታቸው የስደተኞች ችግር በባሰ ሁኔታ ላይ ይገኛል”። ሲሉ አዲሱ የጣልያን መንግሥት አዋጅ የስደተኞችን ችግር እንዳባሰው ገልጸዋል።

ቅዱስ ኣባታችን የስደተኞችና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ድራማ የዓለም ሕዝብ ኣስተያየትና ኅሊና እንዲቀስቅስ እንጸልይ ብሎ ያቀረቡት ጥሪ ግቡ ሊመታ ይችላልን የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ፣ “አዎ ይቻላል። ትኵረታችን በዚሁ ላይ ነው ያለው። ብዙዎች ለዚህ ቅድሚያ በመስጠት የመጀመርያ ጉዳይ የሕይወት ጥያቄ በመሆኑ የመኖርና አለመኖር ጉዳይ ነው፣ ከዛም የዚህ ችግር ሰለባ በመሆን ለሚሰቃዩት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን መብታቸው እንዲጠበቅ ብዙዎች እየተበበሩ ናቸው። ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን በመከላከል፣ በመቀበል እና መብታቸውን በመጠበቅ ልንረዳ እንችላለን በማለት ኅሊና ያለው ሁሉ እንዲጸልይና የተቻለውን እንዲያበረክት ጠየቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.