2009-08-03 15:37:23

ዜና ዕረፍት ኮራዞ ኣኵይኖ


የፊሊፒንስ የቀድሞ ርእሰ ብሔር ኮራዞ አኵይኖ ባደረባቸው የነቀርሳ በሽታ ማኒላ በሚገኘው ሆስፒታል ሲረዱ ቆይተው፣ ከትላትና በስትያ በ 76 ዓመት ዕድሚያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የአገሪቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት RealAudioMP3 አባል የሆነው ልጃቸው በይፋ በማሳወቅ በሕክምና እያገገሙ በነበሩበት ወቅት በጸሎት ካለ ማቋረጥ ትብብራቸውን ላቀረቡት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ቀደም ሲል ኮራዞ አኵይኖ በሕክምና ላይ እያሉ እግዚአብሔር ፈውሱን ይሰጣቸው ዘንድ በጸሎት ቅርብ ሆነው እንደሚሸኙዋቸው የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ታርቺዚዮ ፊርማ የሰፈረበት መልእክት በማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጉዋደንሲዮ ሮሳለስ በኩል በማስተላለፍ እንዳረጋገጡላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ኮራዞ አኵይኖ ለፊሊፒንስ ሕዝብ ነጻነት እና ከአገሪቱ አመጽ፣ አለ መከባበር እና አለ መቀባበል የመሳሰሉት እክሎች ተወግደው፣ ፖሊቲካዊ ሥርዓት የሰፈነበት ዴሞክራሲ እንዲረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉ መሆናቸውም በሁሉም የፖለቲካ አካላት የሚዘከሩ በፊሊፒንስ ሕዝብ የሚናፈቁ መሆናቸውም ይነገራል።

በተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት ለይፋዊ ጉብኝት የሚገኙት የፊሊፒንስ ርእሰ ብሔር ግሎሪያ ማቻፓጋል አሮዮ የቀድሞ ርእሰ ብሔር አኵይኖ ዜና እረፍት እደሰሙ በፊሊፒንስ 10 ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን አውጀዋል። የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጉዋደንሲዮ ሮሳለስ የፊሊፒንስ ሕዝብ ላንድ አፍታ ጸጥታ በማንገስ እግዚአብሔርን በኮራዞ አኵይኖ ለፊሊፒንስ ሕዝብ የሰጠውን ጸጋ ምክንያት ምስጋና እንዲያቀርብ ያደራ ጥሪ ማቅረባቸው ለማወቅ ተችለዋል። እ.ኤ.አ. ኮራዞ አኵይኖ ከ 1986 እስከ 1992 ዓ.ም. ርእሰ ብሔር ሆነው ያገለገሉ የመጀመሪያ ሴት መሪ መሆናቸውም ይዘከራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.