2009-08-03 15:39:20

በክርስትያን ምእመናን ላይ የደረሰው የሞት አደጋ


አንድ ሕጻን አራት ሴቶች የሚገኙባቸው 8 ክርስትያን የፓኪስታን ዜጎች በሚኖሩበት በፑንጃብ አውራጃ በሚገኘው በጎጅራ መንደር የነብሩት በክልሉ በሚገኙት አክራሪያን ሙስሊሞች አንድ ክርስትያን ምእመን RealAudioMP3 ቁራንን የሚያረክስ ድርጊት ፈጽሟል በሚል ሰበብ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ለሞት፣ ሌሎች ባሥር የሚገመቱትን ለቀላል እና ለከባድ የመቁሰል አደጋ መዳረጋቸው ተገለጠ። የፓኪስታን አናሳው የማኅበረሰብ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እክራሪያን ሙስሊሞች በክርስትያኖቹ ላይ የሞት አደጋ ለመጣል ያነሳሳቸው አንድ ክርስትያን ቁራንን የሚያረክስ ተግባር ፈጽሟል በማለት ያቀረቡት ሰበብ ከእውነት የራቀ ሐሰት ነው ካሉ በኋላ የክልሉ የፖሊስ ኃይሎች አናሳውን የክርስትያን ማኅበረሰብ ካደጋ ለማትረፍ ጥረት አላደረጉም ሲሉ ክስ አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በእ.ኤ.አ. በዚህ የወንጌል ግብረ ተልዕኮ አሳብ የሚጸለይበት ወር፣ ስለ ክርስቶስ ስደት፣ ጭቆና መከራ የሚደርስባቸው እና አድልዎ ስለ ሚፈጸምባቸው አናሳ ክርስትያን ማህብረሰብ እንዲጸለይ ለመላ ቤተ ክርስትያን አደራ በማለት የህዝቦች እኵልነት ተረጋገጦ የአናሳው የማህበረሰብ የሰብአዊ መብትና ፈቃድ እንዲከበርጥሪ አቅርበዋል።

የኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ዋና አስተዳዳሪ አባ በርናርዶ ቸርቨለራ፣ የዚህ አይነት ጸረ ክርስትያን ማህበረሰብ አባላት አደጋ የሚደጋገም እና ክርስትያን ማህበርሰብ ባልፍፈጸሙት ወንጀል እየተከሰሱ የሞት ፍርድ እንደሚበየንባቸውም አስታውሰው፣ አናሳው የፓኪስታን ክርስትያን ማኅበረሰብ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋልጦ እንደሚገኝ ገልጠው፣ በ 36 የእስያ ክልል አገሮች የሃይማኖት ነጻነት ውሱን መሆኑም አብራርተው ለተለያዩ ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙም ገልጠዋል።

የፓኪስታን ርእሰ ብሔር አሲፍ አሊ ዛርዳሪ በክርስትያን ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመው በደል፣ የተጣለው የሞት አደጋ አውግዘው የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ጸረ ምስልምና ሃይማኖትና የዚህ ሃይማኖት ትምህርት የሚጻረር ብሔራዊ የአገር ሕግ የሚጥስ፣ ጸረ አገር ተግባር ነው በማለት አደጋው በተጣለበት ክልል የሚገኘው የፖሊስ ጽ/ቤት ስለ ተጣለው አደጋ እንዲያጣራ እና ተጠያቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ይተጉ ዘንድ አሳስበዋል። ይህ በንዲህ እንዳለም የፓኪስታን የአንሳው ማኅበርሰብ ጉዳይ ሚኒ. ሻባል ብሃቲ እና የፓኪስታን የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተሟጋች ማኅበር ሊቀ መንበር ካምራን ሚካኤል አደጋው ለደረሰበት የፓኪስታን ክርስያን ማኅበርስብ ቅርብ መሆናቸው በመግለጥ የተፈጸመው የሞት አደጋ ሲያወግዙ፣ መንግሥት ቤቱንና ንብረቱን ለጋየበት ክርስትያን ማኅበርሰብ ካሳ እንደሚሰጥ አስውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.