2009-08-03 15:23:04

ቅድስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ስፖርተኞችን ተቀብለው አነጋገሩ.

 


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ እዚህ ሮማ ውስጥ አለም አቀፍ የዋና ስፖርት ውድድር ተሳታፊ የሆኑ ስፖርተኞች እና የስፖርት አመራር ባለስልጣናት በካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አዳራሽ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር በዚሁ አጋጣሚ የተገናኙ ስፖርተኞች እና የስፖርት አስተዳዳሪዎች ከአንድ መቶ ሰማንያ ሶስት ሀገራት የተውጣጡ በድምሩ አራት ሺ መኖራቸው መግለጫው አመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ስፖርተኞችን ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ የስፖርት እና የሕይወት ቻምፒዮንስ ትሆኑ ዘንድ እመኝላችሃለሁኝ ፡ ሲሉ መግለጣጫው ገልጠዋል።

በስሜት የሚደረግ እና ሥነ ምግባር የተላበሰ ስፖርት ለአካላዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬ አስፈላጊ እና እጅግ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለስፖርተኞቹ መግለጣቸው በካስተልጋንደልፎ ሐዋርያዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ አዳራሽ የወጣ መግለጫ አስገንዝበዋል።

ቤተክርስትያን ስፖርት የምትከታተለው ሚዛኑየጠበቀ ህንጸተ ሰው እንደሚያስገኝ በመረዳትመሆኑ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መግለጣቸው መግለጫው አክሎ ገልጠዋል።

ቅዱስ መጽሐፍ ጠቅሰውም ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ስፖርት እውነተኛ የሰው እሴት መሁኑ እና የህንጸተ ሰው መሳርያ መሆኑ ማመላከቱ ርእሰ ሊቃነ ፡ጳጳሳት በነዲክቶስ ማመላከቱ ማስታወሳቸው መግለጫው አስገንዝበውል።

በመሠረቱ ስፖርት ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ አዘል የህዝቦች አገናኝ እና እውነተኛ አግባብ ተከትሎ ከተሰራም ወንድማማችነት እና ትብብር ቀስቃሽ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ማስገንዘባቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

በመጨረሻም ሁለት የዋና ስፖርት ቻምፒዮኖች ጀርመናዊ ፓውል ቢደርማን እና የጣልያን ዜጋ ፈደሪካ ፐለግሪኒ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የወርቅ መዳልያ ስጦታ መስጠታቸው ካስተል ጋንደልፎ ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.