2009-07-31 14:28:11

የሞት ፍርድ


ቅዱስ ኤጂዲያ የካቶሊክ ማኅበር የካዛኪስታን መንግሥት የሞት ፍርድ ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እንዲሰረዝ በማድረጉ ምክንያት በሰጠው መገልጫ፣ ባለማችን ስለ ሞት ፍርድ በተመለከተ የተለያዩ አገሮች የሞት ፍርድ RealAudioMP3 ከወንጀለኛ መቅጫ ሕጋቸው ለማንሳት እየወሰዱት ያለው ውሳኔ እና አንዳንድ አገሮች የሞት ፍርድ የተበየነበት አቤት እንዲል የማይፈቅደው ሕጋቸውን በመከለስ እንዳነሱ በመጥቀስ፣ እንዲሁም እንደ አብነት ጃፓንን በመጥቀስ በቅርቡ የሞት ፍርድ በብዛት የተበየነባቸው አገሮች እንዳሉም ማስታወሱ ሲር የዜና አግልግሎት አስታወቀ።

የሞት ፍርድ ከወንጀለኛ መቅጫ ሕጋቸው ባያነሱም’ኳ የሞት ፍርድ ጉዳይ በተመለከተ በተለያዩ አገሮች እየተሰጠበት ያለው ትኩረት፣ በተለያዩ መስኮች የሕይወት ባህል ለማነቃቃት የሚደረጉት የባህል ዘመቻዎችና ጥረቶች የብዙ ዜጎች ፍላጎት ከመሳቡም ባሻገር አልፎ ሕሊናን ጭምር እያነቃቃ ሲሆን ይህ ደግሞ የሞት ፍርድ ባለማችን ተቀባይነቱ እየዛለ መምጣቱ የሚመሰክር መሆኑም የቅዱስ ኤጂዲዮ ማህበር ባወጣው መገልጫ እንዳመለከተ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.