2009-07-31 14:25:39

ናይጀሪያ


ከባለፈው እሁድ ጀምሮ በናይጀሪያ ታሊባን በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው እስላማዊ ጸንፈኞች ያቀጣጠሉት ጸረ ክርስትያን አመጽ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጠ። እነዚህ ሆኮ ሃራም፣ RealAudioMP3 “ህንጸት/ትምህርት ሓጢኣት ነው” በምል መጠሪያ የሚለዩት ታጣቂ ኃይሎች ከናይጀሪያ የጸጥታ ኃይሎች ጋር ያነሳሱት ግጭት ሳቢያ 600 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ። በናይጀሪይ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የእድገት የፍትህ እና የሰላም ተቋም አስተዳዳሪ ኣባ ኦቢዮራ ኢከ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስትያን እንርዳ ከተሰኘው ያለም አቀፍ የግብረ ሠናይ ማኅበር ጋር ባካሄዱት ውይይት “እነዚህ አክራሪያ ሙስሊሞች ያነሳሱት ግጭት በናይጀሪያ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ተገደው ሃይማኖታቸውን በመካድ የምስልምና ሃይማኖት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ ተግባር ነው” ብለዋል።

ይህ በሰሜን ያናጀሪያ ክልል ከባለፈው ሐምሌ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. አክራሪያን ሙስሊሞች ያነሳሱት ግጭት በናይጀሪያ የእስላም ሃይማኖት ሕግ እርሱም ሻሪአ የአገሪቱ ብሔራዊ የመተዳደሪያ ደንብ ይሆን ዘንድ አልሞ የተጀመረ ጥቃት መሆኑ ሲገለጥ፣ አክራሪያን ታጣቂው ኃይል የተለያዩ የናይጀሪይ የፖሊስ ሃይል ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ መሆናቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ ይኽ ከባውቺ የጀመረው ግጭት ወደ ዮበ ካኖ እና ቦርኖ እየተስፋፋ መሆኑ ባሰራጨው ዜና ያመለክታል።

አባ ኢከ ምእራብ አገሮች ናይጀሪያ አክራሪያን ሙስሊሞች ለመግታት ባገሪቱ የተረጋጋ ሰላማዊ ማህበራዊ ኑሮ እንዲረጋገጥ ለምታረማምደው ትግል ደገፋቸውን ያቀርቡ ዘንድ መጠየቃቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አታወቀ። በናይጀሪያ የሻሪያ ሕግ መተዳደሪያ ደንብ በሆነባቸው 12 ግዛቶች ውስጥ የሚኖረው አናሳው ክርስትያን ማኅበረሰብ ለተለያዩ ማሕበራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠው እና ተገለወም እንደሚኖሩ እና በነዚህ ግዛቶች ብዙ አቢያተ ክርስትያናት ወድመዋል ክርስትያኖች ተገደው የምስልምናው ሃይማኖት እንዲቀበሉ በተለይ ደግሞ ሴቶች ለዚህ አደጋ በቀላሉ ተጋልጠው እንደሚገኙ የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.