2009-07-31 14:24:11

በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የወሲብ በደል


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ባለፉት ቀናት ባለማችን ዙሪያ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የወሲብ በደል በተመለከተ የተጠናቀረው ሰነድ ለድርጅቱ የደህንነት እና የጸጥታ ምክር ቤት በይፋ በቀረበበት ዕለት፣ RealAudioMP3 ይኽ ዓይነቱ ክስተት በሚገባ ለመቆጣጠር የሁሉም አገሮች ፍላጎት መሆን አለበት ብለዋል።

በቅርቡ በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ የሰሜን ኪቩ ጎብኝተው የተመለሱት ድንበር አልቦ የሓኪሞች የግብረ ሠናይ ማህበር አባል የስነ ሕክምና ሊቅ ሮዛና ሰስቲቶ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “የወሲብ በደል በብዙ አገሮች በተለይ ደግሞ ግጭት እና ጦርነት በሚካሄድባቸው አገሮች እንደ ጦር መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው”። “ጦርነት፦ አገር አካባቢ ለመቆጣጠር ለመውረር፣ የሚፈጸም ሲሆን፣ ጦርነት በሚካሄድባቸው ክልል ሴቶችን አስገድዶ መድፈር ያንዱም የማንነት መለያውን ለመውረር የሚፈጸም መሆኑ አብራርተው። የግዳጅ ወሲብ ሰለባ የሆነችው ሴት፣ ከማህበረሰብ ተነጥላ በማሕጸንዋ የጠላትን ዘር ተተሸክማለች ተብላ የወሲብ በደል ሰለባ ሆና እያለ፣ ከራስዋ ማኅበረሰብ ተነጥላ እንድትኖር ትገደዳለች፣ አባል በሆነችበት ማኅበረሰብ እና ቤተሰብም ጽያፍ ሆና ትቆጠራለች” ብለዋል።

“ወገኖቿ ይጸየፏታል፣ ተገላም ትኖራለች፣ የዚህ አሰቃቂ ወንጀል ሰለባ የሆኑትን ሴቶች የሚሰጠው የስነ አእምሮ የሕክምና እርዳታ በጣም ወሳኝ ነው፣ ስለዚህ ማህበረሰቡ እንዲሰማት ከሚያደርጋት ሰብአዊ ማህበራዊ እና ስነ አእምሮአዊ ሃፍረት እና ጭንቀት ተላቃ ነጻ እና ጤናማ ዜጋ ሆና እንድትኖር የሚሰጠው ድጋፍ ቀላል አይደለም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.