2009-07-31 14:20:11

ር.ሊ.ጳ. ከበጋ ወቅት ዕረፍት መልስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሰሜን ጣሊያን አኦስታ ሸልቆ ክልል ለስኮምበስ በሚባል መንደር የሁለት ሳምንታት ዕረፍት ካሳለፉ በኋላ ባለፈው ረቡዕ ምሽት ወደ ካስተል ጋንዶልፎ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት RealAudioMP3 የበጋ ወቅት መኖሪያ ሐዋርያዊ አዳራሽ ተመልሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. በካስተል ጋንዶልፎ በፈረንጆች አቆጣጠር እስከ መስከረም ወር መጨረሻ እንደሚቆዩ ሲመለከት፣ እዛም ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት በጸሎት በዕረፍት እና በሽርሽር፣ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሰዎች ጋር በመገናኘት እና አሰተምህሮዎች በመስጠት ላይ ይሆናል። ስለዚህ ቅዱስነታቸው በአኦስታ ሸለቆ ተራራማ

ው መንደር የጀመሩትን የበጋ ወቅት ዕረፍት በካስተልካንዶልፎ ሓይቅ አጠገብ እንደሚቀጥሉበት ታውቀዋል።

ር.ሊ.ጳ. ከሰሜን ጣሊያን የለስኮምበስ መንደር ወደ ካስተል ጋንዶልፎ ከተማ እንደገቡ፣ ለከተማው ነዋሪ ሕዝብ ስላምታ እና ሐዋርያዊ ቡራኬ አቅርበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.