2009-07-31 15:09:31

ሥነ ሕይወት በክርስትያናዊ አመለካከት.


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለፊታችን ዓመት 20010 እኤአ ጥር አንድ ቀን የሚያስተላልፉት ዓለም አቀፍ መልእክተ ሰላም ፡ ሰላም ለማፍራት ከፈለክ አከባቢህን ጠብቅ የተሰየመ መሆኑ በቅድስት መንበር የፍትህ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት አስታውቀዋል።

መልእክተ ሰላሙ የዚች የምንኖርባት ምድር መጻኢ ዕድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ሐለፊነት በመውሰድ እንድትጠበቅ የሚጠይቅ መሆኑ ይታወቃል።

ሰላም ከሰው ክብር እና ከአከባቢ የተሳሰረ መሆኑ የሚያመለክት መልእክተ ሰላም መሆኑንም ተመልክተዋል።

በቅርቡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጻፉት “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ” እውነተኛይቱ ፍቅር በሐቅ ላይ ትገኛለች የተሰየመውን ሓርያዊ መልእክት ስንመለከት መልእክቱ የአከባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጠ መኖሩ የሚታወስ ነው ።

አከባቢ በአግባቡ ካልተያዘ በዓለም ህዝቦች ላይ ሁከት ለመቀስቀስ ስለሚችል ከፍተኛ ትኩረት የሚያሻው መሆኑ ፡ የጠቀሰ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልእክተ ሰላም በህዝቦች መሀከል ፍትሕ እና ትብብር እንደሚያስፈልግ አበክሮ ያሳስባል።

የዛሬ ኅብረተሰብ ለፍጆታ እና ሀብት ለማካበት የሚከተለው የሕይወት ዘይቤ እና አኗኗር ተሐድሶ እና ለውጥ እንደሚያሻው የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ መልእክት እንደሚያመልክትም የሚዘነጋ አይደለም።

ሐዋርያዊ መልእክቱ የዓለም ኅብረተሰብ የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረግ ዓለምን ፍትህ ከሌለ ሰላም ስለማይገኝ ሰላም የነሳት የፍትህ እጦት መሠረታዊ መፍትሔ እንድያገኝለት የሚጠይቅ እንደሆነም የሚታወቅ ነው።

የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ መልእክት የሰው ልጅ በአሁኑ ወቅት በተክኖሎጂ በኩል እጅጉ ባደገበትግዜ ተፈጥሮአዊ ሀብቶች ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግ እንደሚገባው በአጽንኦት የሚጠይቅ መሆኑንም የሚታወስ ነው።

ቤተክርስትያን የፍጥረት ሁሉ ሐላፊነት እንዳላት የሚያመልክት ሐዋርያዊ መልእክቱ ፡ የሰው ልጅ ራሱን በራሱ እያወደመ ችላ ለማለት እንደማትችል ይገልጻል።

ፍጥረት ሁሉ ለመጠበቅ የስነ ምግባር ባለ ቤት የሆነ ማኅበረ ሰብ እንደሚያስፈልግም የሚያሳስብ መልእክት መሆኑም ይታወቃል።

የሰው እና የፍጥረት ሥነ ሕይወቶች ተፈጥሮአዊ ሂደቶች መከተል ሲገባቸው በሰው ሰራሽ ድርጊቶች ሲታወኩ እና የሰው ተፈጥሮአዊ እድገት ስተጓጐል እንደሚታይም ሐዋርያዊ መልእክቱ እንደሚያስገነዝብ ይታወቃል።

ሐዋርያዊ መልእክቱ የተፈጥሮ አያያዝ ሥርዓት ማስተካከል እንደሚያሻው ይጠቁም እና የአከባቢ ተፈጥሮ እንዲጠበቅ በመጠየቅ ፡ የሚቀየሱ ሕጎች ግን ሰብአዊ ክብር ለመታደግ የማይረዱ ስለሚሆኑ ሁለቱም ነገራት ርስ በርሳቸው ተጻራሪ እንደሚሆኑ ይገልጣል።

በክርስትያናዊ አመለካከት ተፈጥሮ እንደአጋጣሚ የተገኘ እና ያለ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስራ መሆኑ ሐዋርያዊ መልእክቱ እንደሚያሰምርበትም ያታወቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.