2009-07-29 15:50:11

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ መልእክት ለጣልያን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቀርበዋል.


 የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ለጣልያን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ እውነተኛይቱ ፍቅር በሐቅ ላይ ትገኛለች የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት ማቅረባቸው ተገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ እንዳመለከቱት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት በህዝብ የተሰጣቸው ዓቢይ ሐላፊነት በሚገባ ለመወጣት ሐዋርያዊ መልእክቱ እጅግ ይረዳቸዋል።

የወቅቱ ሥነ ምግባራዊ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ፈናተዎች ገጥሞ ለማሸነፍ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ መልእክት መልስ እንደሚሰጥ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ መግለጣቸው ተገልጠዋል።

እውነት እና ሐቅ የተሳሰሩ መሆናቸው ያመለከቱ ፡ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ በነሱ በመንተራስ እና ተፈጥሮአዊ ሕግ በማክበር ሐቀኛ እና ሰብአዊ ደስታ ለማግኘት እንደ ሚቻል ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

እውነት እና ሐቅ የተያያዙ በመሆናቸው ለማሕበራዊ ኤኮኖሚ ችግርም መፍትሔ መሆናቸው ብፅዕነታቸው ማመልከታቸው ተገልጠዋል።

የቤተክርስትያን ማኅበራዊ እምነተ ትምህርት እና በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጻፉት ካሪታስ ኢን ቨሪታተ እውነት በሐቅ ላይ ይገኛል የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት ይዘታቸው አንድ ዓይነት መሆናቸው የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ማስገንዘባቸው ታውቆዋል።

የቤተክርስትያን ዶክትሪን ማለት ማኅበራዊ እምነተ ትምህርት እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን የሰው ልጅ ማእከል ያደረገ መሆኑንም ብፅዕነታቸው አስታውሰዋል።

የቤተክርስትያን ማኅበራዊ አንቀጸ ትምህርት ሥነምግባራዊ ጽንሰ ሐሳብ ሳይሆን ሰብአዊ እንክብካቤ ጠያቂ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ አስገንዝበዋል።

ሰብአዊ እድገት ዋስትና የሚያሻው መሆኑ የገለጡት ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ፍትሕ ብቻ እድገቱ ለመረጋገጥ ስለማይችል ወንድማማችነት እና ፈሪሐ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልግ ማመልከታቸው ተገልጠዋል።

የጣልያን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕረስዳንት ረናቶ ስኪፋኒ የቅድስት መንበር ውሳና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በምክር ቤቱ ተገኝተው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ መልእክት ለምክር ቤቱ አባላት በማቅረባቸው ማመስገናቸው ተመልክተዋል።

ጣልያን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕረኢዳንት ረናቶ ስኪፋኒ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት ተስፋ ሰጪ እና በዓለማችን ሰላም ለማስፈን መደረግ ያላባቸውን ጥረቶች የሚያመላክት ስህተት አራሚ መሆኑ ጠቅሰው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን አወድሰው ማመስገናቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.