2009-07-29 14:01:03

የር.ሊ.ጳጳሳት የሰሜን ጣሊያን የበጋ ወቅት ዕረፍት ቆይታ መጠናቀቁ ተነገረ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 እ.ኤ አ ከያዝነው ወርሐ ሓምሌ 13 ቀን ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት በሰሜን ኢጣሊያ አኦስታ ሸለቆ ለስኮምበስ በሚባል መንደር በማሳለፍ የነበሩት የበጋ ወቅት ዕረፍት RealAudioMP3 ጊዜ ዛሬ ሮብ ሐምሌ 29 ቀን መጠናቀቁ ተገለጠ።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ሮብ ማምሻውን ወደ ካስተልጋንዶልፎ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወቅት መኖሪያ ሐዋርያዊ አዳራሽ ከመመለሳቸው በፊት በሰሜን ኢጣሊያ ለስኮምበስ መንደር ለሁለት ሳምንታት ያሳለፉት የዕረፍት ጊዜ እንዲሳካና እንዲቃና ለተባበሩዋቸው የመንግሥትና የቤተክርስትያን ባለሥልጣናት እንዲሁም የፀጥታ ኃይል ሠራዊት ኀላፊዎች እና የለስኮምበስ መንደር ነዋሪ ሕዝብ በሙሉ ከልባቸው አመስግነው ተሰናብተዋቸዋል።

የር.ሊ.ጳጳሳት ቃል አቀባይ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እንዳስታወቁትም የኢንትሮድ ከተማ መስተዳደር ለር.ሊ.ጳጳሳት የከተማዋ የክብር ዜግነት መብት ፈቃድ ለመስጠት ወስኖአል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ማምሻውን በቻምፒኖ ብሔራዊ አየር ማረፊያ በኩል እስከ ፊታችን ወርሐ መስከረም መጨርሻ ወደሚቆዩበት ወደ ካስተልጋንዶልፎ ሓዋርያዊ አደራሻቸው በሰላም ተመልስዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.