2009-07-29 13:36:12

አደንዛዥ እጽዋት በዓለም ዙርያ


በተባበሩት መንግሥታት ያደንዛዥ እጸዋት እና የወንጀል ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት አደንዛዥ እጸዋት በዓለም ዙሪያ በተመለከተ ጥናታዊ ሰነድ ማቅረቡ ተገለጠ። ሰነዱ በይፋ መገልጫ በተሰጠበት ዕለት RealAudioMP3 የጽሕፈት ቤት ተጠሪ አንቶኒዮ ኮስታ አደንዛዥ እጽዋት ጨርሶ ለማጥፋት የዓለም መንግሥታት አቢይ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በኢጣሊያ 362 ሺሕ ሕዝብ የአደንዛዥ እጽዋት ሱሰኛ መሆኑ ከጥናቱ ለመረዳት ሲቻል። ይህ የኢጣሊያው ያደንዛዥ እጽዋት ተጠቃሚው ህዝብ ብዛት በኤውሮጳ ደረጃ ሲታይ ባንደኛ ደረጃ ከምትገኘው ከታላቋ ብሪጣኒያ ቀጥሎ ሁለተኛ መሆኑ ኮስታ ገልጠው፣ የዚህ አደንዛዥ እጸዋት በብዛት ተጠቃሚው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል መሆኑ የጥናቱ ሰነድ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.