2009-07-27 13:53:16

የጀርመን የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር


የጀርመን የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሮበርት ዞሊትሽ እ.ኤ.አ. ከሓምሌ 26 ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ናይጀሪያን እንደሚጎበኙ የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 የሰጠው መግልጫ ያመለክታል።

ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለብሔራዊ ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው ድጋፍ ማጽናት በሚል ቃል የተመራ እንደሚሆንም መግለጫው የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት በማሳወቅ በግኑኝነቱ ወቅትም በናይጀሪያ እየተስፋፋ ስላለው የሃይማኖት አክራሪነት እና የሚያስከትለው ችግር ሰፊ ውይይት በማካሄድ የሚከሰቱት ማኅበራዊ ችግሮች ለመቀረፍ የሚቻልበትን መንገድ በመተባበር ለመቀየስ እና ቤተ ክርስትያን ሰላም ለማረጋገጥ የምትሰጠውን ድጋፍ መሠረት በማድረግ ጥልቅ ውይይት እንደሚያደርጉ የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ዞሊትሽ የጴንጠ ቆስጠ አክራሪ ሃይማኖት መስፋፋት የሚታይበትን የናይጀሪያን ደቡባዊው ክልል እና እንዲሁም አናሳው የካቶሊክ ክርስትያን ምእመን የሚገኝበት የናይጀሪያ ክልል እንደሚጎበኙም ሲር በማሳወቅ እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ካርል ሌህማን ናይጀሪያ ጎብኝተው እንደነበርም ሲር የዜና አገልግሎት በማስታወስ ጠቅሶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.