2009-07-27 15:33:02

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሶስተኛ ሐዋርያዊ መልእክት.


የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ “caritas in veritate” እውነተኛ ፍቅር ሐቅ ላይ የተመረኮሰች ናት የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት ይፋ ከሆነች አስራ አምስት ቀናት ማለፉ የሚታወስ ነው ።

ሐዋርያዊ መልእክቱ በተመለከተም በዓለም ዙርያ ለማለት በምያስደፍር መልኩ ውይይት እንደተካሄደበት እና አስተያየትም እንደተሰጠበት ይታወቃል።

የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በቫቲካን ተለቪዝዮን ማእከል በሳምንት አንድ ግዜ በምያሰፍሩት ርእሰ ዓንቀጽ እንዳመለከቱት፡በተለያዩ ሀገራት እና ቋንቋዎች የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ መልዕክት አዎንታዊ ስሜት አሳርፈዋል።

ዓለማችን በኤኮኖምያዊ እና ፋይናንሳዊ ቀውሶች በምትገኝበት ግዜ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጻፉት ሐዋርያዊ መልእክት ፡ የተስፋ መልእክት መሆኑ ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

የሰው ዘር ያለውን ኃያል ቀውስ ለመግታት ፍትሕ ለማንገስ ኤኮኖምያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ተክህሎ እና መሳርያ እንዳለው ያሚያመለክተው የሐዋርያዊ መልእክቱ ሐረግ ተደናቂነት ማትረፉ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ የቫቲካን ተለቪዝዮን ማእከል እና የራድዮ ቫቲካን ዳይረክተር ያስቀመጡት ርእሰ አንቀጽ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስገንዝበዋል።

የቃል አቀባዩ ርእሰ አንቀጽ እንዳመለከተው፡ እድገት ለሁሉ አገልግሎት ከዋለ ማን ነው ተገልጋዩ የሚለውን ጥያቄ መመለሱ አስፈላጊ ነው ።

አገልግሎቱ ለሰው ሕይወት እንዲሆን እንደሚጠበቅ የቃል አቀባዩ ርእሰ አንቀጽ ያመለክታል።

ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስለ ሰው ያላትን ራእይ ለሰው ዘር ሁሉ እንደምትገልጥ ያመለከተ ርእሰ አንቀጹ የዚህ ምክንያት ለሰው አገልግሎት ያላትን ከፍተኛ አሳቢነት እና ሐላፊነት ስለሆነ መሆኑ ያስገነዝባል።








All the contents on this site are copyrighted ©.