2009-07-27 13:55:58

ዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት


የካቶሊክ የሃይማኖት አንቀጽ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን በመወከል የዓለም ዓቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት አባላት የሚሆኑትን መምረጡ የቅዱስ ማኅበሩ RealAudioMP3 ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ጆሴፍ ለቫዳ አስታወቁ። በዚህ ድርገት ሁለት የጀርመን ዜጎች የሆኑት ዓለማውያን ምእመናን እንዲሁም አንዲት የስዊዘርላንድ እና አንዲት አሜሪካዊት ድንግል ሁለት የኢጣሊያ ዜጎች እነርሱም በጀኖቫ የቲሎጊያ ግብረ ገብ መምህር ኣባ ማርኮ ዲልዲ እና በሚላኖ የመሠረተ ቲዮሎጊያ መምህር ኣባ ፒየርአንጀሎ ሴኪኤሪ የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ባአልነት እንደሚገኙበትን የቅዱስ ማኅበሩ መግለጫ ያመለክታል።

በዚህ ድርገትም የብፁዕ ኣቡነ ብሩኖ ፎርተ እና ብፁዕ አቡነ ኢኛዚዮ ሳና አበይት የቲዮሎጎያ ሊቃውንት ባባልነት እንደሚገኙበትም መግለጫው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.