2009-07-27 15:08:03

ክርስቶስን በተልእኮው መርዳት

 


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እህድ ለበጋው ዕረፍታቸው ከሚገኙበት በለኮምበስ መንደር መኖሪያ ቤታቸው አጠገብ ከሚገኘው አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መምራታቸው እና መንፍሳዊ መልእክት RealAudioMP3 ማስተላለፋቸው ተመለከተ።

ቅዱስነታቸው ትናንትና ዕለቱ የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ቤተ ክርስትያን የቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና የኢየሱስ አያቶች ማለት የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች በዓል መኖሩን አስመልክተው በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት አያቶች ሁሉ ለልጅ ልጆቻቸው በማስተማር ዘርፍ ላላቸው ሓላፊነት እና ለሚሰጡት ከፍተኛ ክቡር አገልግሎት አሞግሰው አመስግነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.