2009-07-27 15:33:20

ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በአመሪካ.


ፊታችን መስከረም ወር በዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የገደማት እና ማኅበራት የበላይ እናቶች የቅዱስ ቁርባን አምልኮ ብሔራዊ ጉባኤ እንደሚያካሄዱ ተገልጠዋል።

ይህ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የተነገረለት መንፈሳዊ ጉባኤ ዋሺንግቶን ውስጥ በሚገኘው የንጽህት ድንግልማርያም ገዳም እንደሚከናወን ይህ ከዋሺንግቶን የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

ብሔራዊ ጉባኤው የፍቅር ቀዋሚመስዋዕት በተሰየመ አርእስት ዙርያ እንደሚወያይ ዜናው አስታውቀዋል።

በዚሁ ብሔራዊ ጉባኤ የሚገኙ የገዳማት የሃይማኖት ማኅበሮች የበላይ ሐላፊዎች እና ምእመናን የክርስትያን ማእከላዊ እሴት በሆነው ቅዱስ ቁርባን ትኩረት ሰጥተው እንደሚወያዩ ሲን ሲ የተባለ ካቶሊካዊ የዜና አገልግሎት የዜና ምንጭ ከዋሺንግቶን አመልክተዋል።

ብሔራዊ ጉባኤው በመስዋዕተ ቅዳሴ የሚከፍቱት የፊላደልፊያ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ጃስቲን ሪጋሊ ሲሆኑ በግግር የሚከፍቱት ደግሞ የዋሺንግቶን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶናልድ ቩረል መሆናቸው የዜና አገልግሎቱ አብራረዋል።

በዜናው መሠረት የቦስቶን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሲን ኦ”ማለይ የባልቲሞር ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዊን ኦ ብራያን በዩናይትድ ስቴትስ የቅድስት መንበር አቡሐዋርያዊ መልእከተኛ ብፁዕነ ፒትየሮ ሳምቢ በዚሁ ብሔራዊ ጉባኤ እንደሚገኙ አብሮ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

ወደ አራት ሺ የሚጠጉ የገደማት እና ማኅበራት የበላይ ሐላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዚሁ ፊታችን መስከረም ዋሺንግቶን ላይ በሚካሄደው ጉባኤ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተጠቁመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.