2009-07-27 13:50:27

ቅዱሳት ኢያቄም እና ሓና


በላቲን ሥርዓት ሐምሌ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማሪያም ወላጆች የቅዱሳት ኢያቄም እና ሓና በዓል መከበሩ ተገለጠ። ስለ በዓሉ እና ለነዚህ ሁለት ቅዱሳት የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች RealAudioMP3 ስለ ሚቀርበው አምልኮ አስመልክተው፣ የስነ ማርያም ሊቀ በጳጳሳዊ ማሪያኑም የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር አባ ኤርማኖ ቲኒዮሎ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ማሪያም ሥጋችን ለብሶ ወደዚህ ዓለም ለማዳናችን የመጣው እግዚአብሔር እናት ነች። ቤተ ክርስትያን ከማትቀበላቸው ወንጌሎች አንዱ የያዕቆብ ወንጌል ስለ ማሪያም መወለድ ሲያወሳ፣ ኢያቄም ባለ ጸጋ እና ሃብታም ሰው ባለ ቤቱ ሓና መኻን በመሆንዋ፣ እግዚአብሔር ረስቶኛል ስትልን እድሜዋ የገፋ በመሆኑም የመውለዱ ዕድሌ አልፎብኛል በማለት ስትሰቃይ፣ እምባዋን በማፍሰስ ወደ እግዚአብሔር ስትቀርብ ኢያቄም አለ ምንም ተስፋ መቁረጥ መልካም ነገሮች እያደረገ ሕይወቱን ሲመራ፣ ቅድስነታቸው የተረዳው እግዝሔር ኢያቄምን በመልአኩ አማካኝነት ጸሎቱን እንደሰማ እና ምንም’ኳ በእድሜ የገፊ ቢሆንም ቅሉ ልጅ እንደሚኖራቸው ተበሰሩ፣ ኢያቄም እና ሓና የማርያውም ወላጆች ለመሆን እንደበቁ” ይገልጥልናል።

እ.ኤ.አ. በስድስተኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ የቅዱሳት ኢያቄም እና ሓና ባሲሊካ ተመሠረተ፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም በዓለ ጽንሰታ ለማርያም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 9 መከበር ተጀመረ ይህ ደግሞ ቆይቶ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ማሪያም አለ አዳም ሓጢአት መጸነስዋን በእምነት እና በአንቀጸ ሃይማኖት ተደንግጎ የንጽሕት ድንግል ማርያም በዓል ሆኖ መከበር ተጀመረ፣ በምስራቅ አቢያተ ክርስትያን በዓሉ የሚከበርበት እለት ዕለት አንዳልተለወጠም አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.