2009-07-27 13:45:14

መንግሥታዊ ቀውስ በሆንዱራስ


በሆንዱራስ የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ስኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የተፈጸሙት የመንግሥት ግልበጣ ሴራ ያስከተለው መንግሥታዊ ቀውስ እና ውጥረት ባለበት የጸና እንደሚመስል ይነገራል። በተካሄደው የ RealAudioMP3 መንግሥት ግልበጣ ሴራ ከሥልጣናቸው የተነሱት በኒካራጉዋይ በስደት ላይ የሚገኙት ርእሰ ብሔር ማኑኤል ዘላያ ወደ አገራቸው የተመለሱ እንደሆነ በቀጥታ ለእስር እደሚዳረጉ በተፈጸመው የመንግሥት ግልበጣ ሴራ አማካኝነት የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ሆነው ያሉት ሚከሌቲ ቀደም ሲል ማሳወቃቸው የሚዝከር ሲሆን፣ ዘላያ ወደ አገራቸው ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ባለፈው ቅዳሜ አገራቸው ከኒካራጉዋ ጋር በሚያዋስነት የድንበር ክልል ለተወሰኑ ሰዓት ቆይታ ማድረጋቸው ሲነገር፣ ይህ የፈጸሙት ተግባር ባገሪቱ ተከስቶ ያለው ፖሊቲካዊ ቀውስ ሊያባብሰው እንደሚችል ተገምተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሥልጣናቸው የተገለበጡት የርእሰ ብሔር ዘላያ ደጋፊዎች ሰላማዊ ሰልፍ አድማ ማካሄዳቸው ሲገለጥ። የጸጥታ ኃይሎች አድመኞችን ለመበተን በወሰዱት እርምጃ ሳቢያ አንድ በአድማይ ይሳተፍ የነበረ ያገሪቱ ዜጋ ለሞት መዳረጋቸው ተገልጠዋል። በዚህች አገር ተከስቶ ያለው ውጥረት አሳሳቢ መሆኑ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ሂላርይ ክሊንተን በመግለጥ፣ ውጥረቱ ባንድ የጋራ ስምምነት እቅድ መሠረት ይወገድ ዘንድም ጠይቀዋል።

በሆንዱራስ ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻለው ሕገ መንግሥት በማክበር መሆኑ የስነ ላቲን አሜሪካ ሊቅ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ልዊስ ባዲላ ገልጠው የሆንዱራስ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ደጋግሞ እያቀረበው ያለው ውሳኔ መሆኑም አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.