2009-07-24 15:57:34

የማኅበረ ልኡካን አባል አባ ሩይቨን ሐዋርያዊ ወኪል ተሰየሙ.


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የማኅበረ ልኡካን ማኅበር አባል አባ ተኦደሩስ ፋን ሩቨን በኢትዮጵያ የነቀምት ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ መሰየማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

አባ ተኦደሩስ ፋን ሩቨን በኔዘርላንድ የአምስተርዳም ሀገረ ስብከት ሪስቪክ በተባለ ቦታ ግንቦት ሀያ ሁለት ቀን 1938 የተወለዱ በ1964 ፓኒንገን በተባለ ቦታ መዓርገ ክህነት የተቀበሉ መሆናቸው መግለጫው ገልጠዋል።

አባ ተኦዶሩስ ፋን ሩቨን መዓርገ ክህነት ከተቀበሉ ከአንድ ዓመት በኃላ በማኅበረ ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ የተላኩ እና ሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የቤተክርስትያን ሐዋርያዊ ሙያ የተሰማሩ መሆናቸው መግለጫው በተጨማሪ አመልክተዋል።

እስከ አሁን ድረስም የጂማ ቦንጋ ሐዋርያዊ አሰተዳዳሪ ሆነው መስራታቸው መግለጫው አክሎ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.