2009-07-24 13:41:22

በሩሲያ የሥነ ሃይማኖት ትምህርት ዳግም መፈቀድ


በሩሲያ የዛሬ 92 ዓመት በፊት ተቋርጦ የነበረው የሥነ ሃይማኖት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ዳግም መታከሉ ተገልጠዋል። ይኽንን ጉዳይ በተመለከተ በሞስኮ የእመ አምላክ ካቴድራል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ፓውሎ ፐዚ ከቫቲካ ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ RealAudioMP3 ፣ የሥነ ሃይማኖት ክፍለ ጊዜ ለሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን የሚመለከት ቢሆንም ቅሉ፣ በአገሪቱ ለሚገኙት አናሳ ሃይማኖትች ዕድል የሚሰጥ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።

አዲሱ የሩሲያው መንግሥት ውሳኔ አናሳ ሃይማኖቶችን በቀጥታ የሚመለከት ባይሆንም ቅሉ የአናሳው ሃይማኖት ተከታዮች አብላጫ በሆኑበት የግል ትምህርት ቤቶች በሚሰጠው የሥነ ሃይማኖት ትምህርት በስፋት እግምት እንደሚሰጠው እና ተቀዳሚው የዚህ የስነ ሃይማኖት ትምህርት ዓላማ የሰው ልጅ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማእከል በማድረግ የሚቀርብ እንደሚሆንም ብጹዕ ኣቡነ ፐዚ ገልጠዋ። የኮሙኒዝም ሥርዓት ወድቀት የተለያዩ ሕዝቦች ለተለያዩ ዓበይት ችግሮች እንዳጋለጠም የሚዘከር ሲሆን፣ ሃይማኖት ሕዝባዊ ሱስ የሚለው የማርክስ ንድፈ ሓሳብ መሠረት የሌለው መሆኑ ከተረጋገጠ ወዲህ፣ የህዝቦች ዳግም ወደ ሃይማኖት መመለስ ጥማት እና ሩጫ በትክክል መመራት ይኖርበታል፣ ወደ ሃይማኖት ለመመለስ ያለው ፍላጎት ከእምነት ጋር ላያገናኝ ይችላል፣ ስለዚህ ተፈላጊው መሠረታዊው ጉዳይ ወደ እምነት መመለስ ነው፣ በሩሲያ የሃይማኖት ሥነ ትምህርት ዳግም በትምህርት ያሰጣጥ ደንብ እንዲታከል ያስገደዱ ምክንያቶች ሥነ ምግባራዊ፣ ግብረ ገባዊ መነሻ ያላቸው መሆኑም ገልጠው፣ በሩሲያ ይህ አዲሱ የትምህርት ደንብ በቀጥታ ለካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚመለከት ባይሆንም ቅሉ የሩሲያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚህ ዘርፍ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነች በለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.