2009-07-22 12:57:04

የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት


በአኅጽሮት ቃል አያ በመባል የሚታወቀው የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በጦር እና በዘር ማጥፋት ወንጀል በተከሰሱት በቀድሞ የሰርቢያ ቦስኒያ መሪ ራዶቫን ካርድዚች በወንጀለኛነት ፍርድ ለመበየን ቀዳሚ ችሎት መክፈቱ ተገለጠ። RealAudioMP3

እኚህ እ.ኤ.አ. በ90ዎች ዓመታት በሰርቢያውያን እና በሌሎች ጎሳዎች እልቂት ፈጽመዋል የሚባሉት ካርዲዝች በሰርቢያ ቦስኒያ ዩጎዝላቪያን መከፋፈል ምክንያት የሆነው ተካሂዶ በነበረው ጦርነት የነበራቸው ሚና ምን እንደሚመስል፣ ሁከቱ ተቀጣጥሎ በነበረበት ወቅት ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉት ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ማርዞማኞ ከቫቲካ ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ካርዲዝች ፣የራስዋን ልኡላዊነቷን በራሷ አውጃ ለነበረችው የቦስኒያ ረፓብሊካዊት ሰርቢያ ርእሰ ብሔር በመሆንና ከሳቸውም ጋር ራትኮ ምላዲች የጦር አዛዥ በመሆን ሁኔታውን ለመቆጣጠር የተወሰዱት ፖሊቲካዊ ውሳኔዎች፣ እርሱም አንድ እስላም አማኝ የማይኖርባት ቦስኒያ ለማረጋገጥ ዓልሞ የተወሰዱት እርምጃዎች በቀጥታ እሳቸውን የሚመለከት መሆኑ ገልጠው፣ ሳራየቮን ለሺሕ ቀናት በመውረር የተፈጸመው እልቂት እንዲሁም በ 1995 ዓ.ም. በስረብረኒካ እርሱም በኤውሮጳ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመው የሰው ዘረ እልቂት በትክክል ከ 6 ሺሕ እስከ 7 ሺሕ ሕዝብ ለሞት የተዳረገበት ውሳኔ ቀዳሚ ተጠያቂ ናቸው” ካሉ በኋላ “ካራድዚች ከሰርቢያ ባለሥልጣናት ጋር ጥብቅ ግኑንነት እንደነበራቸውም አስታውሰዋል”።








All the contents on this site are copyrighted ©.