2009-07-22 15:10:17

የኤውሮጳ አብያተ ክርስትያናት አጠቃላይ ጉባኤ.


በፈረንሳ ሊዮን ከተማ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው የኤውሮጳ አብያተ ክርስትያናት አጠቃላይ ስብሰባ መጠቃለሉ ከዚሁ ቦታ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ሰብሰባው ኦርቶዶክስ አንገሊካዊት እና የፕሮተስታንት አብያተ ክርስትያናት ያቀፈ መሆኑ ይታወቃል።

ከስብሰባው ፍጻሜ በኃላ የወጣ መግለጫ ጠቅሶ ሲር የተባለ የዜና አገልግሎት እንዳመልከተው ክርስትያን እንደመሆናችን መጠን ለሁሉም ነገር ተስፋ ማድረግ እንሻለን ። የአብያተ ክርስትያናቱ ልዑካን በአጠቃላይ የዓለም በተለይ የወቅቱ የኤውሮጳ ሁኔታ በተመለከተ መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን ፡ተስፋ ማድረግ ደስታ ሰላም እና ትባት ይሰጠናል በማለት በአጠቃላይ መግለጫው ማውሳታቸው የዜና አገልግሎቱ አስታውቀዋል።

ሙሉ አንድነት እና ዕርቅ የተጐናጸፈች ኤውሮጳ እውን ትሆን ዘንዳ አብያተ ክርስትያናቱ አበክረው ለመጣርም እንደተግባቡ ተገልጠዋል።

ኤውሮጳ ውስጥ የተለያዩ ሀገራት ሃይማኖቶች እና ባህሎች በነፃ በጋራ እና በሰላም የሚኖርባት ኤውሮጳ ማየት እንደሚፈልጉ በዚሁ በፈረንሳ ሊዮን ከተማ ላይ የተሰበሰቡ የአብያተ ክርስትያናት ልዑካን መግለጣቸውም ተመልክተዋል።

የአብያተ ክርስትያናቱ ልዑካን ኤውሮጳ ውስጥ በእገር በቅክ እና ስደተኞች በሀብታሞች እና ድሆች ስራ ባላቸው እና የሌላቸው ሰዎች መካከል መቀራረብ እንጂ መራራቅ እንዲገታ መብታቸው በሚጠበቅላቸው እና የማይጠበቅላቸው ሰዎች ማየት እንደማይፈልጉ በመግለጫቸው ላይ ማስፈራቸው ሲር የዜና አገልግልት አስገንዝበዋል።

ለፍትህ ለሰላም እና ብልጽግና ለስብአዊ መብቶች ክብር እንደሚቆሙም ባወጡት መግለጫ አስምረውበታል ሲል የዜና አገልግሎቱ አክሎ አመለክተዋል።

ክርስትያን ዘወትር ተስፋ አለው ተስፋ አይቆርጥም ሲባል ፡ እጅ አጣምሮ ተስፋ ማድረግ ሳይሆን እምነት ላይ በመመርኰዝ ተጨባጭ አዎንታዊ ርምጃዎች መውሰድ ማለት መሆኑንም በመግለጫው መካተቱ ተነግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.