2009-07-22 15:11:03

የኢራን ፖሊቲካ እና ሽኩቻ.


በኢስላም ረፓብሊክ ኢራን ባለፈው ሰነ ወር አስራ ሁለት ቀን ድህረ ፕረሲዳንታዊ ምርጫ የተከሰተው የፖሊቲካ ትርምስ ባለበት እንደቀጠለ መሆኑ ተመልክተዋል።

የቀድሞ የሀገሪቱ ፕረሲዳንት መሐመድ ካታሚ የምርጫው ውጤት ሕጋዊ መኖሩ እና አለመኖሩ ረፈረንደም ተካሄዶ የህዝብ ውሳኔ እንድሰጥበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

የዚሁ አወዛጋቢ ፕረሲዳንታዊ ምርጫ አሸነፊ አሕመዲነጃድ መሆናቸው ይፋ ቢነገርም የተወዳዳርያቸው የሁሰይን ሙሳቪ ደጋፊዎች የምርጫው ትክክልነት አጥላልተው በመተቸት እና አደባባይ በመውጣት ቅሬታች አውን ያሰሙ ሲሆን ከፖሊስ ጋር በተካሄደው ግጭትም የተገደሉ እና የሞቱ ተሰላፊዎች መኖራቸውም አይዘነጋም።

ይሁን እና የህዝብ ውሳኔ ይሰጣል አይሰጥም የሚወስኑ የሀገሪቱ የሃይማኖት የበላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ካመነይ ሲሆኑ ፡ እሳቸው ለግርግሩ እና ሁከቱ ባለቤት የምዕራብ ሀገራት መንግስታት ናቸው ባይ እንደሆኑ ከተህራን የደረሰ ዜና ገልፀዋል።

ሌላው የኢራን መንግስት ፕረሲዳንት የነበሩ ራፍሳንጃኒ በበኩላቸው ውጤቱ በማውገዝ ፡ የህዝብ ፈቃድ የሌለው መንግሥት ሕጋዊ መሆን እንደማይችል መግለጫ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ሀገሪቱ ውስጥ በወግ አጥባቂዎች ስልጣን ላይ ባለው መንግስት እና የፖሊቲካ ተሀድሶ ፈላጊዎች መሀማድ ካታሚ እና ሌሎች መካከል ቀደም ሲል የተጀመረው ሽኩቻ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ አብሮ የደረሰ ዜና ያመልክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የብራዚል መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ሉይዝ ኢናጽዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከምርጫው በኃላ ኢራንን በመጐብኝት የመጀመርያ መሪ እንደሚሆኑ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.