2009-07-22 15:09:51

ኤች አይ ቪ ኤይድስ ትኩረት የሰጠ ስብሰባ በደቡብ አፍሪቃ ረፓብሊክ.


በደቡብ አፍሪቃ ረፓብሊክ ኬይፕ ታውን ላይ በኤች አይ ቪ ኤይድስ ዙርያ አምስተኛ ስብሰባ መከፈቱ ተመልክተዋል።

በዚሁ በከይፕ ታውን የተጀመረው ቀሳፊ ሕመሙ ትኩረት የሰጠ ስብሰባ የህክምና ጠበብት የሳይንስ ምሁራን የፖሊቲካ ሰዎች እና የመንግስት ያልሆኑ ተቋሞች ተወካዮች በአጠቃላይ አምስት ሺ ልኡካን እየተሳተፉ መሆናቸው ተገልጠዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት በ2007 እኤአ በኤች አይ ቪ ኤይድስ ሁለት ሚልዮን ሰዎች መሞታቸው መሞታቸው፡ ሳላሳ ሶስት ሚልዮን ደግሞ ከነዚህ ሀያ ሁለት ሚልዮን የሚሆኑ ከሰሀራ በታች በሚገኙ ሀገራት በዚሁ ሕመም እንደተለከፉ ይህ ከይፕ ታውን የደረሰ ዜና አስታውሰዋል።

በየዓመቱ ሁለት ሚልዮን ሰባት መቶ ሺ ህዝብ በዚሁ ሕመም እንገሚያዙ ያመለከተ ዜና በ2001 እኤአ በኤች አይ ቪ ኤይድስ የተለከፉ ሰዎች ከሶስት ሚልዮን እንደሚበልጡ አመልክተዋል።

ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ቀውስ ቢኖርም ጸረ ኤይድስ የተጀመረው ትግል መገታት እንደሌለበት ያመለከተ ዜና እንደሚያመልክተው በቅርቡ በጣልያን የተሰበሰቡ የቡድን ስምንት በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት መሪዎች ሕመሙ ለመግታት ፋይናንሳዊ እገዛ ባለ ማድረጋቸው የስብሰባው ተሳታፊዎች ቅር መሰኘታቸው ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጠዋል።

ከሁሉም በላይ በዚሁ ሕመም የተጠቃችው አፍሪቃ ክፍለ ዓለም መሆንዋ እና በክፍለ ዓለሚቱ ሕመሙ ለማስታገስ የሚገዙ መድኀኒቶች እየተሟጠጡ መሆናቸው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ማኅበር ተወካዮች መማረራቸው ይህ ከከይፕ ታውን የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል ።ረፓብሊክ ደቡብ አፍሪቃ በዚሁ ደዌ በእጅጉ ከተጠቁ ሀገራት አንዋ እንደሆነችም ተወስተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.