2009-07-22 13:00:14

ብራዚል፣ “ፍቅር በሐቅ”


የብራዚል ብፁዓንRealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 “ፍቅር በሐቅ” በሚል ርእስ በደረስዋት ዓዋዲት መልእክት ዙሪያ አስተያየት ማቅረቡ ተገለጠ። የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት “የቅዱስ አባታችን ቃላቶች ጥበብ የተካነው የሰውን ልጅ አዕምሮና ሕሊናን የሚያነቃቃ ልማት የሁሉም ሰው ዘር ጥሪ መሆኑ በማብራራትም ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የ RealAudioMP3 ተፈጠር መሆኑና ይኸንን የላቀውን ክብር እግምት ውስጥ ያስገባ ግብረ ገብ እና ስነ ምግባር ኖሮት በሕቅ ላይ የጸና መደጋገፍ መተባበር መከተል እንደሚገባው የምታስረዳ የምታሳስብ እና ይኸንን ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት በተጨባጭ የምታስተምር ዓዋዲት መልእክት ነች” እንዳለ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ

የብራዚል ብሔራው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጀራልዶ ልይሪዮ ሮቻ “የሚምንም ይሁን የማያምን ሁሉ ችላ ሊለው የማይገባው ሀሳብ የሰፈረባት አዋዲት መልእክት መሆኗ በመጥቀስ ልማት እና እድገት ለሰው ልጅ ጥቅም ያተኮረ፣ አለ ልዩነት እና አድልዎ ሰውን ማእክል ያድረገ መሆን እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን በደረስዋት ዓዋዲት መልእክት በማብራራት ቤተ ክርስትያን ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ለመፍታት ሞያዊ መፍትሔ የማታቀርብ ቢሆንም ቅሉ በወንጌል ጥበብ ተመርታ መፍትሔ የሚሻውን የሰውን ልጅ አእምሮን ታነቃቃለች” እንዳሉም ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.