2009-07-22 13:04:08

ሶማሊያ


RealAudioMP3 የሶማሊያ አክራሪያን ሙስሊሞች በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ተልእኮና የዚህ ተልእኮ ሠራተኞች አገልግሎት እንቅፋት መሆናቸ ተገለጠ። አል ሻባብ በሶማሊያ ያልቃይዳ የቀኝ እጅ ነው የሚባለው ኃይል ባይዶአና ዋጃድ አካባቢ በሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤቶች ላይ ባስከተሉት ችግር ሳቢያ፣ ባይዶአ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርጫፍ ጽ/ቤት መዘጋቱ ሲነገር፣ አክራሪያኑ በሶማሊያ ለሚገኙት የግብረ ሰናይ ማኅበራት እንቅስቃሴ እና አገልግሎት መሰናክል መሆናቸው ተገልጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአል ሻባብ የታገቱት ሁለት የፈረንሳይ የደህንነትና የጸጥታ ኃይል አባላት ጉዳይ ምንም የታወቀ ነገረ እንደሌለ ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.