2009-07-22 13:07:26

ስፖርት ስነ ምግባርንና ኣብነታዊ ትምሀርትን ማክበር  መቀጠል  እንዳለበት ተነገረ


ቅ.አ.ር.በነዲክቶስ 16 ‘ቱር ደ ፍራንስ’ በመባል ለሚታወቀው የብስክሌት እሽቅድድም ውድድር አትሌቶች ቡድን የሰላምታ መልእክት ማስተላለፋቸው ተመለከተ። RealAudioMP3

የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ውድድር በፈረንሣይ ጀምሮ በጎረቤት አገራት በማለፍ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ማይልስ ርቀት በመሸፈን በሃያ አንድ ቀናት ጊዜ የሚጠናቀቅ በየዓመቱ የሚደረግ የብስክሌት አትሌቾች ስፖርታዊ ውድድር ነው።

የር.ሊ.ጳጳሳት ቃል አቀባይና የቫቲካን ረዲዮ ሓላፊ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ር.ሊ.ጳጳሳት ለዕረፍት ከሚገኙበት ከሰሜን ጣሊያን የአኦስታ ሸለቆ መንደር ለቫቲካን ረዲዮ በስልክ በሰጡት መግለጫ የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ውድድር አትሌቶች ቡድን ትናንት በስዊዘርላንድ በኩል ወደ ጣሊያን አገር ገብቶ ር.ሊ.ጳጳሳት ለዕረፍት ከሚገኙበት የለኮምበስ መንደር ማለፉና ር.ሊ.ጳጳሳት እስፖርት ለሁለንተናዊው ሰብአዊ እድገት መስጠት የሚችለውን ትልቅ አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት ስፖርት ምን ጊዜም ከስነ ምግባርና አርአያነት ከማስተማር ሞያ መነጠል እንደሌለበት በማስገንዘብ ለተሳታፊዎቹ ልባዊ ሰላምታና የመልካም እድል ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል ሲሉ አረጋግጠዋል።

የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ውድድር በአከባቢው ልዩና ተወዳጅ እንዲሆን ያደረገው የእሽቅድድሙ የመጀመሪያው አሸናፊ አትሌት ማውሪቸ ጋሪን የአኦስታ ሸለቆ ተወላጅ በመሆኑና ስፖርቱ በአከባቢው መንደሮች ሲያልፍ ከስድሳ ዓመታት በኋላ ዘንድሮ በመሆኑ ነው ሲሉ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አክለው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.