2009-07-21 16:51:10

ርአሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ እና ጨረቃ.


ከአርባ ዓመታት በፊት እኤአ 1969 ሶስት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች አርምስትሮንግ አልድሪን እና ኮሊንስ የተባሉ ጠፈርተኞች ለመጀመርያ ግዜ እግራቸው ጨረቃ ላይ ማኖራቸው የሚታወስ ሲሆን ከስድስት መቶ ሚልዮን ህዝብ በላይ አስደናቂ ሁኔታው መመልከታቸው የሚታወስ ነው፡

ድርጊቱ ሰብአዊ እውቀት አዲስ ምዕራፍ የከፈተበት መሆንም የማይዘነጋ ነው።

በዚያው ግዜ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ጳውሎስ ስድስተኛ ሐምለ ሀያ ቀን 1969 እኤአ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከደገሙ በኃላ ዛሬ ለሰው ዘር ሁሉ አንድ ትልቅ ታሪካዊ ነው ማላታቸው ትናንትና የቫቲካን ቃ እቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገልጠዋል።

ቃል አቀባዩ በተጨማሪ እንዳመልከቱት ፡ ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የድርጊቱ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ተሳታፍነታቸው በማሳየት የሰው ልጅ ብርታት እና ብልሃት አድንቀዋል።

አያይዘውም በዓለም አከባቢ የነበሩት ጦርነቶች እና የምግብ አንስተኛነት እንዲቀረፉ ማሳሰበቻው የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውሰዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ጠፈርተኞቹ ወደ ጨረቃ ከማቅናታቸው ከጥቂት ግዝያት በፊት “populorum progressio የህዝቦች እድገት የተሰኘ ሐዋርያዊ መልዕክት ለኅትመት አብቅተው መኖራቸው ቃል አቀባዩ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.