2009-07-21 16:42:41

ብፁዕ ካርዲናል ጆዮቫኒ ላዮሎ በኡክራይን.


በቅድስት መንበር የቫቲካን ጳጳሳዊ ኮሚስዮን ፕረሲዳንት ብፁዕ ካርዲናል ጂዮቫኒ ላዮሎ በየኡክራይን ቤተክርስትያን የተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ሀገሪቱ ይፋ ለመጐብኘት ትናንትና ለኦፖሊ ከተማ መግባታቸው ቫቲካን አስታውቀዋል።

በዚሁ ቫቲካን ያወጣው መግለጫ መሠረት ብፁዕ ካርዲናል ጂዮቫኒ ላዮሎ ዛሬ ረፋድ ላይ ከተማይቱ ውስጥ በሚገኘው ካተድራል መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

በቅድስት መንበር የቫቲካን ጳጳሳዊ ኮሚስዮን ፕረሲዳንት ብፁዕ ካርዲናል ላዮሎ በኡክራይን ቆይታቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ሀገረ ስብከት እንደሚጐበኙ እና ከወጣቶች ጋር እንደሚገናኙ ተመልክተዋል።

የቫቲካን መግለጫ እንዳመለከተው፡ ብፁዕ ካርዲናል ጂዩቫኒ ላዮሎ ከለኦፖሊ ግሪኽ ካቶሊካዊ መትሮፖሊታን እና ከብፁዕ ካርዲናል ሁሳር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ላዮሎ እንደገለጹት በዚሁ ግድ የለሽነት በሚታይባት ዓለም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ተጠምረን እምነታችን በደስታ እና አንድነት ለመግለጽ በመቻላችን ደስታ ይሰማኛል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.