2009-07-20 14:11:20

ሶማሊያ


በሶማሊያ ያለው ውጥረት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ሲገለጥ፣ ባለፈው ለሌት ኬኒያ ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስነው ስሜናዊ ምስራቅ ክልል፣ በሚገኘው የማንደራ ክልል ሦስት ላንድ የፈረንሳይ የግብረ ሠናይ ማኅበር አባላት RealAudioMP3 እነርሱም የዙምባብዌ የፓኪስታን እና የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥት ዜጋ የሆኑት መታገታቸው ተገለጠ። እንደሚባለም ከሆኑ የጠለፋው ባለ ቤት በሶማሊያ ላልቃይዳ የቀኝ እጅ ተብሎ የሚነገርለት አል ሻባብ በመባል የሚታወቀው አማጽያን ኃይል መሆኑ ሲታወቅ፣ የታገቱት ወደ ሶማሊያ ክልል ሳይወስዱ እንዳልቀረም ይነጋራል።

ይህ በንዲህ እንዳለም ባለፈው ማክሰኞ በሞቃዲሹ የታገቱት ሁለት የፈረንሳይ የደህንነት ኣባላት ነጻ ለማስለቀቅ ካጋቾች ጋር ሙሉ ግኑኝነት እየተደረገ ነው ባይባልም ቅሉ ግኑኝነት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ የፈረንሳይ መንግሥት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ክላውደ ጉኤአንት አስታውቀው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ትላትና አጋቾቹ ባሰራጩት መገልጫ መሠረት ግን ሁለቱ ታጋጆች በሻሪኣ፣ እስላማዊ ሕግ መሠረት ለሕግ እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።

የተከናወነው ግብረ ጠለፋ የሶማሊያ የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆኑ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት እና በፈረንሳይ ወህኒ ቤት የሚገኙት የሶሊያ የባህር ወንበዴዎች አባላትን ለመበቀል ያቀና መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ በባህር ወንበዴዎች እጅግ ተጠልፋ የነበችው 11 ባሕረኞች ያሳፈረች ይጀርመን የንግድ መርከብ ነጻ ስትለቀቅ ሌላ ባጋቾቹ እጅ ያለቸው የጀርመን መርከብ ነጻ ለማስለቀቅ ድርድሩ ግና እየቀጠለ መሆኑም ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.