2009-07-20 14:14:26

ማውሪታኒያ


በማውሪታኒያ ሕዝባዊ ምርጫ መካሄዱ ሲገለስጥ። እ.ኤ.አ. ባለፈው 2008 ዓ.ም. በማውሪታኒያ ተካሂዶ የነበረው የመንግሥት ግልበጣ የመሩት የአገሪቱ የርእሰ ብሔር ሥልጣን የጨበጡት ጀነራል ሞሃመድ ኡልድ አብደላዚዝ RealAudioMP3 በ 51.6% እየመሩ መሆናቸው ማንነታቸው እንዳይገለጥ አደራ ካሉት የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ቢሮ የድምጽ ቆጠራ ተከታታይ ቢሮ ሠራተኞች ከሰጡት ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።

ለምርጫው የቀረቡት አራቱ ተቃዋሚዎች ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያገሪቱ የምርጫ ተቆታጣሪ ኮሚቴ የተካሄደው ምርጫ ውድቅ እንዲያደርገው በመጠየቅ፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም የተካሄደው ምርጫ ሕጋዊነቱን የሚያጣራ አንድ አጣሪ ቡድን ይመለምል ዘንድ መጠየቃቸው ታውቀዋል።

ከመንግሥት ግልበጣ ማግሥት፣ ባገሪቱ ሁከትና ውጥረት እንዳይባባስ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲካሄድ የገላጋይነት ሚና የተጫወቱት የሴነጋል መንግሥት እና አረብ ሊግ መሆናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ የተካሄደው ምርጫ ለመቆጣጠርም ከአፍሪካ ኅብረት እና ከኤውሮጳ ህብረትም ጭምር የተወጣጡት በጠቅላላ 250 ታዛቢ አካላት መላካቸውም ሲገለጥ፣ ምርጫው በተካሄደበት ዕለት በአንዳንድ የርእሰ ከተማይቱ ክልሎች ውጥረት መታየቱም ከማውሪታኒያ የተሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.