2009-07-20 14:17:24

መልካም ነገር ለሚሠሩት እግዚአብሔር ሁሌ ይረዳቸዋል


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ለበጋው ወቅት ዕረፍት በሚገኙበት በአልፕሱ ተራራ መንደር ቤታቸው ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ምሽት ባጋጠማቸው የመንሸራተት አደጋ በቀኝ እጃቸው መጠነኛ ትንሽ ስብራት ደርሶባቸው RealAudioMP3 ዓርብ ጥዋት በቀዶ ህክምና አጥንቱ ገጥሞ እንደታሰረላቸው ከቦታው የር.ሊ.ጳጳሳት ቃል አቀባይ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ፈደሪኮ ሎምባርድ ማስታወቃቸው ተምልክቶአል።

እንደዜናው መሠረት ቅዱስነታቸው ወድያውኑ ከሆስፒታል ተመልሰው መደበኛ የዕረፍት ፕሮግራማቸውን ኢያከናወኑ ሲሆን ስለ አደጋው የሰሙ ብዙ ምእመናን የቤተክርስቲያንና የመንግሥት ኀላፊዎች የመልካም ምኞትና የጸሎት መልእክታት አስተላልፈውላቸዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው ትናንት እሁድ ጥዋት በሄሊኮፕተር ወደ ቅ.መንበሩ ዋና ጸሐፊያቸው ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ትውልድ ከተማ በሮማኖ ካናቨዘ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን ሄደው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትና መንፈሳዊ መልእክት ለምእመናን አሰምተዋል፣ ከሥርዓቱ በኋላም በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ቤተሰብ በተደረገላቸው የምሳ ግብጃ ተሳትፈዋል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ትናንት ለምእመናን በአስትላለፉት መልእክት የዓለማችን ኤኮኖሚ ቀውስና የሥራ ቦታ እጦት ብዙ ቤተሰቦችን ችግር ውስጥ ከቶ ኢያሰቃየ መሆኑን አስታውሰው በቅርቡ የዘረጉት ዐዋዲ መልእክት የሚመለከታቸው ሁሉ ዓለምን ለማደስና ለመለወጥ እንዲያነቃቃቸው ተስፋቸው የላቀ መሆኑን ገልጸው እግዚአብሔር ፍትሕን በማክበር እና ራስ ወዳድነትን በማራቅ መልካም ነገር ለሚሠሩት ሰዎች ሁሌ እንደሚረዳቸው አረጋግጠው አንድ ቀን ሁኔታው ተለውጦ እድገትና መሻሻል ሰለሚመጣ ተስፋ መቍረጥ እንደሌለባቸው በአንጻሩ ግን በወንጌል ጸጋዎች የተመራ ሕይወት ለመኖር እድዲችሉ አደራ ብለዋቸዋል።

በመጨርሻም ወጣቶችም ቤተክርስትያን ቅዳሴንና ክርስትያናዊ ባህልን በመውደድ የወንጌል ሕይወት እዲመሩ ከግዜው ፈተናዎችና መሰንክሎችም እንዲጠንቀቁ መክረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.