2009-07-20 14:05:49

ሆንዱራስ


በሆንዱራስ የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ስኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በፈጸመት የመንግሥት ግልበጣ ሳቢያ ከስልጣናቸው የተነሱት በስደት ላይ የሚገኙት ርእሰ ብሔር ማኑኤል ዘላያና እናRealAudioMP3 ያገሪቱ ጊዚያዊ ርእሰ ብሔር ሮበርቶ ሚከለቲ፣ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት በጋራ የሰላም ውይይት እንዲፈቱት የኮስታ ሪካ ርእሰ ብሔር ኦስካር አሪያስ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ሲገለጥ RealAudioMP3 ። ትላንትና ከሥልጣናቸው የተነሱት ርእሰ ብሔር ዘላያ እና ጊዚያዊ የሆንዱራስ ርእሰ ብሔር ሚከለቲ ወኪሎች በርእሰ ብሔር አሪያስ ገላጋይነት ተገናኝተው መወያየታቸው ቢገለጥም ቅሉ ላገሪቱ ሰላም መረጋገጥ የዘላያ ዴሞክራሲያዊው መንግሥት በሥልጣን መመለስ የሚል ሐሳብ የሰፈረበት አሪያስ ያቀረቡት የሰላም እቅድ ወታደራዊ ኃይል በፈጸመው የመግሥት ግልበጣ ሴራ የርእሰ ብሔር ኃላፊነት የተረከቡት ሚከለቲ እንደማይስማሙበት በመግለጣቸውም ይህ በአገሪቱ ተከስቶ ያለው ውጥረት ባለበት እንዲቀጥል ማድረጉ ይነገራል።

በተለያዩ ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ቀውስ በተከሰተባቸው አገሮች በገላጋይነት ሚና አቢይ አስተዋጽዖ የሰጠው እና አመርቂ ውጤትም ያስገኘው የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ ማኅበር መሥራች የታሪክ ሊቅ ፕሮፈሶር አንድረያ ሪካርዲ፣ በሆንዱራስ ተከስቶ ስላለው ፖለቲካዊ ቀውስ በማስመልከት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የውጥረቱ መፍትሔ ይላሉ፣ “አመጽን ባመጽ ለመቅረፍ የማይቻል የታሪክ ገጠመኝ መሠረት የሚካሄድ የሰላም ውይይት መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ውይይት እንጂ አመጽ ግጭት መቼም ቢሆን መፍትሔ ሆኖ አያውቅም” ብለዋል። “እውነተኛው ውይይት ሲባል፣ አንዱ ያንዱን ሀሳብ ለማዳመጥ ተደማምጦም የጋራ መፍትሔ መሻት እንጂ ግትርነት የተሞላው የውይይት መድረክ መሆን የለበትም እንዲህ ካልሆነ ግን ውይይት ገና ሳይጀመር ተበትነዋል ማለት ነው” ብለዋል።

“ብዙውን ጊዜ ሕዝብ በፖለቲካው ዓለም ላይ ያለው እማኝነት ኮሳሳ እየሆነ በመምጣቱም፣ ባገር ጉዳይ ላይ ያለው ተሳታፊነት እየዳሸቀ፣ በራስ ሕይወት ላይ ብቻ ሲጠመድ ይታያል፣ ስለዚህ የፖሊቲካው ዓለም የሕዝብ ድምጽ ማዳመጥ ለሕዝብ እና ለአገር ጥቅም ያቀና መሆን ይገባዋል” ካሉ በኋላ፣ “በሆንዱራስ ተከስቶ ያለው ፖሊቲካዊ ውጥረት በውይይት መድረክ ብቻ ነው ሊፈታ የሚችለው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.