2009-07-18 09:31:09

የዒራቅ ሁከት ፖሊቲካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ አለመሆኑ ተገለጠ፡


በዒራቅ የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂን በንጃሚን ስለይማን በእስፓኛ ማድሪድ ላይ በሀገሪቱ ካሪታስ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ፡ ዒራቅ ውስጥ በመከሄድ ላይ ያለው ግጭት ሁከት እና ብጥብጥ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖሊቲካዊ መሆኑ መግለጣቸው ዘኒት የተባለ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።

ሆኖም ባለፍት ቀናት ሀገሪት ውስጥ በካቶሊካውያን አብያተክርስትያናት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የዒራቅ ክርስትያን ሀገሪቱ ለቀው እንዲሰደዱ ማስገደዱ ብፁዕ አቡነ ጂን በንጃሚን ስለይማን መግለጣቸው የዜና አገልግሎቱ አስታውቀዋል፡ በወቅቱ ግማሽ ሚልዮን ክርስትያን ዒራቅ ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በባቅዳድ ሞሱል እና ኪርኩክ አብያተክርስታናት ላይ የተፈጸመው ጥቃት በአክራሪዎች ተደራጅቶ ሆን ተብሎ የተፈጸመ አሉታዊ ተግባር መሆኑ ብፁዕ አቡነ ስለይማን ማድሪድ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው የዜና አገልግሎቱ ገልጠዋል።ጥቃቱ በአገሮች አቀፍ ማኅበረሰብ መወገዙ የሚታወስ ነው።

ችግር ላይ ለወደቀ ህዝብ የሚንከባከብ የጀርመን የግል ድርጅት የግል ድርጅቶች ሁሉ ዒራቅ ውስጥ ለተፈናቀሉ ወደ ሲርያ እና ዮርዳኖስ ለተሰደዱ ዒራቃውያን አሰቸኳይ ርዳታ እንድያቀርቡ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው።

ዒራቅ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በተከሰተው አስከፊ ፖሊቲካዊ ኤኮኖምያው እና ማኅበራዊ ሁኔታ በርካታ የዒራቅ ዜጎች ለስደት ማቅናታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ብፁዕ አቡነ ስለይማን እና የዒራቅ ካሪታስ ዳይረክተር ናቢል ኒሳን በአሁኑ ግዜ ዒራቅ ውስጥ ያለውን ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች በተመለከተ ለየስፓኛ ካሪታስእና የተረድኦ ድርጅቶች ማስረዳታቸው ዘኒት አስገንዝበዋል።

የዒራቅ ማኅበራዊ እና ክልላዊ ክፍፍል እስካለ ድረስ ብሔራዊ ዕርቅ ይደረጋል ተብሎ ማሰብ እስቸጋሪ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ስለይማን መግለጣቸው ተመልክተዋል።

በአሁኑ ግዜ የዒራቅ ካሪታስ ሀገር ውስጥ ለተፈናቀለ ህዝብ ሰብአዊን እና የሕክምና ርዳታ እየሰጠች መሆንዋ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ስለይማን ሁኔታው በየግዜው አስከፊ እየሆነ መምጣቱ ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።

በግጭቱ የተነሳ የዒራቅ የህክምና ተቋሞች በመፍረሳቸው ቢያንስ ሶስት ሺ አዲስ ክሊኒኮች እና በርካታ መድኀኒቶች እንደምያስፈልጉ የዒራቅ ካሪታስ ዳይረክተር ናቢል ኒሳን በበኩላቸው መግለጣቸው ዘኒት አክሎ አም አልክተዋል።

አርባ በመቶ የሕክምና ባለሙያዎች ሀገሪቱ ለቀው ስለወጡ የሐኪሞች እና የአስተማሚዎች እጥረት መኖሩም ዳይረክተሩ በተጨማሪ መግለጣቸው ታውቆዋል።

የዒራቅ ሁከት ከመካከለኛው ምስራቅ ፖሊቲካዊ ችግር መተሳሰሩ በባቅዳድ የላቲን ሥርዓትሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂን በንጃሚን ስለይማን ጠቅሰው ጥምረታዊ መፍትሔ እንደሚያሻ ማሳሰበቻው ተነግረዋል።

የዒራቅ አክራሪዎች ተጠናክረው ጥቃት እየፈጸሙ መሆናቸው ያመለከቱ ብፁዕ አቡነ ስለይማን ጥቃቱ ለመግታት ኃይል ብቻ ሳይሆን ብልሃት እንደሚጠይቅ ማሳሰባቸውም አብሮ የመጣ ዜና አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.