2009-07-17 13:08:10

ግሪክ


ባለፉት ቀና በግሪክ ፓትራስ አካባቢ የነበረው ግዚያዊ የስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኞች መጠላይ ሠፈር ካገልግሎት ውጭ እንዲሆን በመደረጉ ምክንያት በዚህ መጠለያ የነበረው የስደተኛና የጥገኛው ችግር እጅግ እንዲወሳሰብ ማድረጉ አለ ድንምበር የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሐኪሞች የግብረ ሠናይ ማኅበር አስታወቀ።

በመጠለያው ሠፈር የነበሩት 44 ሕጻናት ኮኒትሳ ወደ ሚገኘ RealAudioMP3 ው መጠለያ ሠፈር ሲላኩ፣ የተቀሩት ስደተኞች ማንነታቸውን ለመለየት በፓትራስ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች በዚሁ ክልል ወደ ሚገኘው ጊዚያዊ መጠለያ ሠፈር ተወስደዋል።

የተባብሩት መንግሥታት የስደተኞችና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት አለ ድንበር የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሐኪሞች ማኅበር የሰጠው አስተያየት በመደገፍ፣ ስደተኞች የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑና ይህ ደግሞ ያስተርጓሚዎች እጥረት እንዳለና ብዙውን ጊዜ ስደተኛው ስለ ራሱ ጉዳይ የሚወሰነው ውሳኔ በሚገባ ሳይረዳው ሲቀበልም እንደሚታይ በመግለጥ፣ በጣም አሳሳቢ ሆኖ ያለው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ የሚያቀርብ ያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ካላገኘ አቤቱታ የማቅረብ መብቱ የአገሪቱ መንግሥት ባጸደቀው አዲስ የስደተኛ መቆጣጠሪያና ማስተዳደሪያ ደንብ አማካኝነት እንዲነሳ በማድረጉ ምክንያት ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.