2009-07-17 13:09:34

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት


የተባበሩት መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የኢራቅ ዳግመ ግንባታ እና ልኡላዊነቷ የተረጋገጠ ዴሞክራሲያዊት አገር ለማድረግ ስለ ሚደረገው ጥረት ለመወያየት እ.ኤ.አ. ሓምሌ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. የኢራቅ መራሔ መንግሥት RealAudioMP3 አል ማሊኪ ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥት ቃለ አቀባይ ሮበርት ጊብስ አስታውቀዋል።

ጊብስ በሰጡት መግለጫም ግኑኝነቱ በኢራቅ ስለ ተሰማራው የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት የመከላከያ ኃይል ከኢራቅ ማስወጣት ስለ ሚባለው ውሳኔ እንዲሁም የሁለቱ አገሮች በባህል በኤኮኖሚ መስክ ያለውን የጋራ ግኑኝነት ለማሻሻል ጭምር ውይይት እንደሚደረግበት ታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሺዒቶች ዓቢይ በዓል ምክንያት በኢራቅ የጸጥታውና የደህንነት ቁጥጥር በበለጥ እንዲያይል መደረጉ ሲነገር፣ ትላትና ጧት በባግዳድ በፍንዳታ አደጋ ሳቢያ 18 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.