2009-07-17 13:01:18

የልማት መስክ የሚከተለው ሥርዓት ሥር ነቀላዊ ክለሳ ያሻዋል


የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ፣ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ” ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ የደረስዋት አዋዲት መልእክት በማስደገፍ ለቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ RealAudioMP3 “የአዋዲቷ መልእክት ማእከል የሰው ልጅ ሕይወት እና ስለ ኅብረተሰብ የሚመለከቱ ዓበይት ጥያዌዎች የምትዳስስ መሆኗ በመጥቀስ፣ ለሁሉም ጥቅም የሚበጅ አመርቂ ውጤት እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የምታነቃቃ ነች” ብለዋል።

ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት አዋዲት መልእክቷን በጥንቃቄ እና በጥልቅ ፍላጎት እንዳነበቡዋት በማመልከት “ያለም አቀፍ ኤኮኖሚ እና የልማት ጉዳይ በኅብረተሰብ ዘንድ እያስከተለው ያለው የመጪው ሕይወት ሥጋት፣ መወላወል እና መጠራጠር የኤኮኖሚው ጉዳይ የምትዳስስ እና የሰብአዊ ግኑኝነቶች በሥራው እና በልማት መስክ እየታየ ያለው ግብታዊ ለውጥ ስለ ተፈጥሮ ያካባቢ ጉዳይ ፈጽሞ የማያልቅ ነው ተብሎ ግምት ይሰጠው የነበረው የተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ በተመለከተ እየታየ ያለው ሥር ነቀል ለውጥ በመዘርዘር፣ ሰው ካምሳያው ጋር ያለውን ግኑኝነት የስነ ሰብ ጥያቄ እይሆነ በመምጣት ላይ ያለው የኅብረተሰብ ጥያቄ በመዳሰስ የሕይወት ገጽታዎች የሰው ልጅ ተግባር ጠለቅ ባለ መልኩ በማስረዳት፣ ኤኮኖሚ በተመለከተም ትርጉሙና ፍጻሜው የሚከተለው ሥርዓት ከተመኩሮ አንጻር የሚጠይቀው ተሃድሶ፣ አርቆ አሳቢ የልማት ሥርዓት በመሳሰሉት መሠረታዊ ጉዳዮች አቢይ እና ጥልቅ አስተንትኖ የሠፈረባት ዓዋዲ መልእክት መሆኗ ለመገንዘብ መቻላቸው በመግለጥ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምስጋናን አቅርበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.