2009-07-17 13:52:43

ር.ሊ.ጳጳሳት የኀዘን መልእክት ላኩ


186 መንገዶኞችን አሳፍሮ ወደ አርመኒያ ርእሰ ከተማ የርቫን በመብረር ላይ ሳለ የካስፒያን አየር መንገድ አይሮፕላን ባለፈው ሮብ ኳዝቪን በተባለ ቦታ በድንገት ወድቆ መከስከሱ የኢራን መንግሥት ባለሥልጣናት RealAudioMP3 ማስታወቃቸው የተመለከተ ሲሆን በአደጋው የአይሮፕላኑ ሠራተኞችና አሳፍሮአቸው የነበረው መንገደኞች በሙሉ መሞታቸው ተገልጦአል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ስለ አደጋው እንደሰሙ በቅ.መንበሩ ዋና ጸሐፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በኩል በኢራን የቅ.መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን ለሚያገለግሉት ለብፁዕ አቡነ ጃን ፖል ጎበል ለኢራን መንግሥትና ሕዝብ በተለይ ደግሞ የአደጋው ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች በሙሉ ኀዘናቸውንና መንፈሳዊ ቅርበታቸውን የሚገልጥ ተለግራም መላካቸው ታውቆአል።

ቅዱስነታቸው በላኩት የኀዘን ተለግራም በአደጋው ለሞቱት ዘላለማዊ ዕረፍት እንዲሁም በኀዘን ላይ ላሉት ቤተሰቦች እግዚአብሔር ጽናቱንና ኃይሉን እንዲሰጣቸው እንደሚጸልዩ አረጋግጠዋል








All the contents on this site are copyrighted ©.